እንደዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጤ እረክቶ አያውቅም፡፡ ፡፡፡ ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ዋናው መልእክት የ EOTC ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ጥጠሚ አብይ አህመድ ትላንት ለካቢኔው የተናገራቸውን ስህተቶች አንድ በአንድ ነቅሶ አውጥቷል:: ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች:- 1- ህገወጡን ሲኖዶስ ከህጋዊው ሲኖዶስ ጋር አቻ አድርጎ ማቅረብ - ስህተት 2- ጉዳዩ ቀላል በድርድር የሚፈታ ነው ያለው (ከባድ ቀኖናዊ ጥሰት በመኾነኑ) - ስህተት 3- ሁለት ፓትርያርክ ሃገር ላይ ነበር ያለው - ውሸት 4- ትግራይ ጳጳስ ተሹሞ ፣ ሲኖዶስ ተቋቁሞ ነበር ያለው - ውሸት 5 - ባለፈው 4ዓመት ለ EOTC ተሰጠ ያለው መሬት - (ቤ/ክ already በስሯ ላሉ ለይዞታዋ ህጋዊ ካርታ ነው የወሰደችው) - ውሸት 6- ጠ/ሚው በግልፅ ለህገወጡ ስብስብ ድጋፍ ማሳየቱ ፣ መንግስት ህጋዊ እውቅና ላለው የቤ/ክ ሲኖዶስ ህግ በማስከበር መተባበር ሲገባው .. በተቃራኒ ቆሞ ህገወጦችን ማገዙ ፣ አባቶችን ማዋከብ ና ማሰሩ - ህገወጥ 7- በቋንቋ መጠቀምን በተመለከተ ቤ/ክ ላይ ያቀረበው ክስ .. በኦሮምኛ ቋንቋ መገልገል ብቻ ሳይኾን መፅሃፍትም እንደታተሙ ፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም እደተከፈቱ ፣ ህገወጥ ተግባር ላይ ያሉትም ሰዎች በዚችው ቤ/ክ የተሾሙ እንደነበሩ በመጥቀስ - ውሸት እንደኾነ አሳይቷል:: 1.2K viewsየኤፍሬም እይታዎች, 20:33