Get Mystery Box with random crypto!

✞በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ✞ በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋና ደስታ እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ ተስ | የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

✞በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ✞

በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ(፪)

ያለቀሱ ሁሉ ይስቃሉ አይቀርም
ይለዋውጠዋል ጌታ መድኃኔዓለም
ማንም ያላሰበው ያልጠበቀውን ድል
ለኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
ማንም ያልጠበቀውን ያልገመተውን ድል
ለኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
      አዝ = = = = =
ሰዎች ቢጠበቡ ገንዘብ ለመሰብሰብ
ይጠላለፋሉ ባልጠበቁት መረብ
እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ
ክፋትና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ
       አዝ = = = = =
ድሆች አስለቅሶ ግፍ የሚሰበስብ
ምን ይመልስ ይሆን ጌታ ፊት ሲቀርብ
ለዚህች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ
አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ
     አዝ= = = = =
የእህል ሽታ ጠፍቶ መሶቡም ቢራቆት
ተስፋችን ሙሉ ነው እኛስ በጌታ ፊት
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ከሠራን በኋላ በጸሎት እንበርታ

             መዝሙር
   ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
☞https://t.me/ephremvi
https://t.me/ephremvi

"እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ"
             ማቴ ፳፰ ፥ ፳