Get Mystery Box with random crypto!

ኃይል የእግዚአብሔር ነው እስከ ዛሬ የሰራናቸው ነገሮች ሁሉ ብሎም የተሻገርናቸው ችግሮች ሁሉ በእ | 21ኛው Century መልዕክት

ኃይል የእግዚአብሔር ነው

እስከ ዛሬ የሰራናቸው ነገሮች ሁሉ ብሎም የተሻገርናቸው ችግሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ሀይል መሆኑን ልናስተውል ይገባል ፤ ሰው በኃይሉ ልበረታ አይችልምና

ወደ ፊትም በእኛ በኩል የምሰሩ ነገሮች በእግዚአብሔር ኃይል መሆኑን እና እግዚአብሔር እኛን ተጠቅሞ እየሰራ እንደሆነ እናስተውል

አንታበይ ፣ በራሳችን አንመካ ፤ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ ተፅፏልና

" እግዚአብሔርም ጌዴዎንን። ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል። እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።"
(መጽሐፈ መሳፍንት 7:2)

ስለዚህ እኛ አቅም እንደለለን በማመን ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር ኃይል መሆኑን እንወቅ

ብዙ ነገር ከተማርኩት ጥቂቱ

Source : ነገ በትልቅ ስፍራ ከምጠብቀው ሰው


@EneFikeDorm