Get Mystery Box with random crypto!

ebstv worldwide📡☑️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebstvworldwide — ebstv worldwide📡☑️ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebstvworldwide — ebstv worldwide📡☑️
የሰርጥ አድራሻ: @ebstvworldwide
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.04K
የሰርጥ መግለጫ

Welcome to EBS TV WORLDWIDE Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates. Don’t forget to share it with your friends.
@ebstvworldwidebot
@EbswhatsnewBot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2023-04-13 20:59:29

1.3K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:48:59 #አሜሪካ
አሜሪካ በየመን ላለፉት 9 አመታት የቀጠለው ጦርነት እንዲቆም እና ዘላቂ የሰላም ስምምነት እንዲደረስ የተጀመረው ጥረት አበረታች ደረጃ ላይ መሆኑን አደነቀች ።

የአሜሪካዉ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ጃክ ሱሊቫን ከሳዓዲ አረቢያው ልዑል መሐመድ ሰልማን ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት በየመን ጦርነት እንዲቆም ሳኡዲ አረቢያ ከየመን የሀውቲ አማፅያን ጋር የጀመረችው ድርድርን ዋሽንግተን እንደምታደንቅ እና ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል ።
የአሜሪካ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣን ሪያድ እና የሀውቲ አማፅያን የጀመሩት ድርድር ፍሬአማ መሆኑን እና በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ የሰላም ስምምነት ይደረሳል ብለው እንደሚያስቡ ነው የተነገረው፡፡
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡

#ጣሊያን
ጣሊያን ወደ ሀገሯ የሚጐርፉ ሕገ ወጥ ስደተኞችን ለመግታት ይረዳኛል ያለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጓን ይፋ አደረገች ።

የጂኦርጂ ሜሎኒ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለ6 ወራት የሚፀና እና በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኩል የሚገቡ ህገ ወጥ ስደተኛችን ወደ የመጡብት አገር እንዲመለሱ የሚያደርግ እና በደቡባዊ የጣሊያን ወደቦች የተከሰተውን የስደተኞች መጨናነቅ ችግር የሚፈታ ነው ተብሏል።
የጣሊያን መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚገባ ተፈጻሚ ለማድረግ ያስችለው ዘንድ 5 ሚሊየን ዩሮ በጀት መመደቡን አስታውቋል።
የጣሊያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአምናው ተመሳሳይ አመት አንጻር በፈረንጆቹ 2023 ብቻ 31 ሺ በላይ ህገ ወጥ ስደተኞች ወደ ጣሊያን መግባታቸውን አረጋግጧል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው ።

#ማላዊ
የማላዊ ፕሬዚዳንት "ፍሬዲ " የተባለው አውሎ ነፋስ የዛሬ ወር ባደረሰው አደጋ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺ ማሻቀቡን አስታወቁ ።

የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻካዌራ በሁለት አስርተ አመታት ውስጥ እጅግ በከፋው "የፍሬዲ " አውሎ ነፋስ ምክኒያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺ ሲያሻቅብ በአደጋው ግማሽ ሚሊየን ህዝብ ተፈናቅሏል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ባጋጠመው በዚሁ አደገኛ አውሎ ነፋስ 2 ሚሊየን ሰዎች ለጉዳት ሲዳረጉ በርካታ የመሰረተ ልማቶች እንዳልነበሩ ሆነው ወድመዋል ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል ።
"ፍሬዲ " የተሰኘው አውሎ ነፋስ ከማላዊ ባሻገር ሞዛምቢክ እና ማዳጋስካርን ክፉኛ መምታቱ በዘገባው ተመልክቷል።

#አሜሪካ
ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያው " ሊንክ ዲን " የኩባንያዎች ሰራተኞች ሆነው የማህበራዊ ሚዲያው ተጠቃሚ ለሆኑ የደንበኞቹ አካውንቶች የሰማያዊ ባጅ በነፃ ሊሠጥ መሆኑ ተሰምቷል።

የሊንክ ዲን ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚሰሩበት ኩባንያ ኢሜል ፣ የክሊር ፕላትፎርምን ወይንም የማይክሮ ሶፍት ኩባንያን
'' አንትራ " አገልግሎት በመጠቀም የሊንክድን አካውንታቸው የሰማያዊ ባጅ እንዲኖረው በነፃ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

የሊንክድን ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የማህበራዊ ገፁ ተጠቃሚዎች አካውንታቸው ሰማያዊ ባጅ እንዲኖረው መደረጉ በተለይ በሚኖራቸው የስራ ግንኙነት መተማመንን የሚፈጥር እና መጭበርበርን የሚያስወገድ ነው ብለዋል ።
ከስራ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ዝነኛ የሆነው የሊንክዲን ማህበራዊ የትስስር ገፅ 4ሺ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የሆኑ የትሰስር ገፁ ተጠቃሚዎች የሊንክዲን አካውንታቸው የሰማያዊ ባጅ እንዲኖረው በቀጥታ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ዘገባው የዘቨርጅ ነው ።
1.5K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:48:48
#አሜሪካ
አሜሪካ በመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ላይ ስለላ ስታካሂድ እንደነበር ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ሾልኮ የወጣ አንድ ሰነድ አመለከተ።

የአሜሪካ የስለላ ተቋማት እለት በእለት የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንቅስቃሴን ሁሉ ይከታተሉ እንደነበር እና የባይደን አስተዳደር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሩሲያ ጥቅም ለማስከበር ፈቃደኛ ናቸው ብሎ እንደሚያምን ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር አፈትልኮ የወጣ መረጃ ያሳያል ተብሏል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በቢቢሲ የተጠየቁት የአሜሪካው የብሔራዊ ደህንነት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ ይሄ አደገኛ ሰነድ ነው ጉዳዩን እያጣራን ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
1.5K viewsedited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:26:12

1.3K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:08:05

1.5K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:07:31

1.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:06:51

1.2K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:59:07 #ግብፅ
ግብፅ 40ሺ ሮኬቶችን አምርታ ለሩሲያ ልትልክ አቅዳ እንደነበር ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ያፈተለከ ነው የተባለው አንድ ሚስጥራዊ መረጃ ይፋ አደረገ፡፡

ዋሽንግተን ፖስት አየሁት ባለው ሚስጥራዊ ሰነድ ግብፅ 40ሺ ሮኬቶችን ለሩስያ ለማምረት ማቀዷ እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ ሮኬቶቹ ሲፈበረኩና ወደ ሩሲያ ሲላኩ በምስጢር እንዲከናወን ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበር ነው የተነገረው፡፡
ይሁንና ግብፅ እቅዷን ለማስፈፀም በተግባር ያሳየችው አፈፃፀም እንደሌለ ነው የተዘገበው፡፡

የግብፅ አንድ ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ምላሽ ካይሮ በሩሲያ - ዩክሬን ጦርነት አንዱን ሀገር ደግፋ ሌላውን ተቃውማ አለመቆሟን ና ለሩሲያ ሮኬቶች ልትልክ አቅዳ ነበር የተባለውም ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።
ከአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስቴር ያፈተለከው ሚስጥራዊ ሰነድ በኢንተርኔት አማካኝነት ተሰራጭቶ በርካቶች መረጃዎቹን እየተቀባበሉት እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

#ሶማሊያ
የመንግስታቱ ድርጅት ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በድርቅ ክፉኛ ለተጐዳችው ሶማሊያ የአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪውን አቀረበ፡፡

በሶማሊያ ጉብኝት ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐሙድ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ በሰብዓዊ ቀውስ እየተፈተነች ላለችው ሶማሊያ የለጋሽ ሀገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተማፅነዋል።
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡

#ኩዌት
የኩዌት የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የበለፀገች ምናባዊ ዜና አንባቢ ይፋ ማድረጉ ትኩረትን ስቧል፡፡

የኩዌት ታይምስ መገናኛ ብዙሃን ንብረት የሆነው የኩዌት የቴሌቪዥን ጣቢያ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገች '' ፌዳ " በመባል የምትጠራ ዜና አንባቢ ጥቅም ላይ ማዋሉ ነው ትኩረትን የሳበው ።
በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የበለፀገችው '' ፊዳ " የምትባለው ዜና አንባቢ አሁን አሁን በመላው ኩዌት ታዋቂ እየሆነች መምጣቷ ተነግሯል፡፡
ዘገባው የሚድል ኢስት አይ ነው፡፡
1.9K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:58:55
#ዩክሬን
ዩክሬን በሩሲያ ላይ ልታካሂድ ያቀደችው የመልሶ ማጥቃት ውጤታማነት ላይ አሜሪካ ስጋት እንዳላት ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ያፈተለከ አንድ ሚስጥራዊ ሰነድ አመላከተ፡፡

ዩክሬን ከገጠማት የጦር መሳሪያዎች እጥረት እና የወታደራዊ ስልጠናዎች ክፍተት ጋር በተያያዘ ኪየቭ በሩሲያ ላይ ልታካሂደው ያቀደችው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ፍሬያማ ይሆናል ብላ እንደማታምን ነው ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ሾልኮ የወጣው ሰነድ ያስረዳው፡፡
የዋሽንግተን ባለስልጣናትም የመልሶ ማጥቃቱ ውጤታማ እንደማይሆን እምነታቸውን የገለጹ ሲሆን ዩክሬን የተሟላ የአየር መቃወሚያ ሥርዓት የሌላት በመሆኑ ለሩሲያ ጥቃት ተጋላጭ እንደሆነች ሚስጥራዊ ሰነዱ ያብራራል፡፡
ዘገባው የዎል ስትሪት ጆርናል ነው ።
1.9K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 21:12:38

1.3K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ