Get Mystery Box with random crypto!

#አሜሪካ አሜሪካ በየመን ላለፉት 9 አመታት የቀጠለው ጦርነት እንዲቆም እና ዘላቂ የሰላም ስምምነት | ebstv worldwide📡☑️

#አሜሪካ
አሜሪካ በየመን ላለፉት 9 አመታት የቀጠለው ጦርነት እንዲቆም እና ዘላቂ የሰላም ስምምነት እንዲደረስ የተጀመረው ጥረት አበረታች ደረጃ ላይ መሆኑን አደነቀች ።

የአሜሪካዉ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ጃክ ሱሊቫን ከሳዓዲ አረቢያው ልዑል መሐመድ ሰልማን ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት በየመን ጦርነት እንዲቆም ሳኡዲ አረቢያ ከየመን የሀውቲ አማፅያን ጋር የጀመረችው ድርድርን ዋሽንግተን እንደምታደንቅ እና ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል ።
የአሜሪካ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣን ሪያድ እና የሀውቲ አማፅያን የጀመሩት ድርድር ፍሬአማ መሆኑን እና በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ የሰላም ስምምነት ይደረሳል ብለው እንደሚያስቡ ነው የተነገረው፡፡
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡

#ጣሊያን
ጣሊያን ወደ ሀገሯ የሚጐርፉ ሕገ ወጥ ስደተኞችን ለመግታት ይረዳኛል ያለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጓን ይፋ አደረገች ።

የጂኦርጂ ሜሎኒ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለ6 ወራት የሚፀና እና በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኩል የሚገቡ ህገ ወጥ ስደተኛችን ወደ የመጡብት አገር እንዲመለሱ የሚያደርግ እና በደቡባዊ የጣሊያን ወደቦች የተከሰተውን የስደተኞች መጨናነቅ ችግር የሚፈታ ነው ተብሏል።
የጣሊያን መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚገባ ተፈጻሚ ለማድረግ ያስችለው ዘንድ 5 ሚሊየን ዩሮ በጀት መመደቡን አስታውቋል።
የጣሊያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአምናው ተመሳሳይ አመት አንጻር በፈረንጆቹ 2023 ብቻ 31 ሺ በላይ ህገ ወጥ ስደተኞች ወደ ጣሊያን መግባታቸውን አረጋግጧል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው ።

#ማላዊ
የማላዊ ፕሬዚዳንት "ፍሬዲ " የተባለው አውሎ ነፋስ የዛሬ ወር ባደረሰው አደጋ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺ ማሻቀቡን አስታወቁ ።

የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻካዌራ በሁለት አስርተ አመታት ውስጥ እጅግ በከፋው "የፍሬዲ " አውሎ ነፋስ ምክኒያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺ ሲያሻቅብ በአደጋው ግማሽ ሚሊየን ህዝብ ተፈናቅሏል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ባጋጠመው በዚሁ አደገኛ አውሎ ነፋስ 2 ሚሊየን ሰዎች ለጉዳት ሲዳረጉ በርካታ የመሰረተ ልማቶች እንዳልነበሩ ሆነው ወድመዋል ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል ።
"ፍሬዲ " የተሰኘው አውሎ ነፋስ ከማላዊ ባሻገር ሞዛምቢክ እና ማዳጋስካርን ክፉኛ መምታቱ በዘገባው ተመልክቷል።

#አሜሪካ
ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያው " ሊንክ ዲን " የኩባንያዎች ሰራተኞች ሆነው የማህበራዊ ሚዲያው ተጠቃሚ ለሆኑ የደንበኞቹ አካውንቶች የሰማያዊ ባጅ በነፃ ሊሠጥ መሆኑ ተሰምቷል።

የሊንክ ዲን ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚሰሩበት ኩባንያ ኢሜል ፣ የክሊር ፕላትፎርምን ወይንም የማይክሮ ሶፍት ኩባንያን
'' አንትራ " አገልግሎት በመጠቀም የሊንክድን አካውንታቸው የሰማያዊ ባጅ እንዲኖረው በነፃ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

የሊንክድን ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የማህበራዊ ገፁ ተጠቃሚዎች አካውንታቸው ሰማያዊ ባጅ እንዲኖረው መደረጉ በተለይ በሚኖራቸው የስራ ግንኙነት መተማመንን የሚፈጥር እና መጭበርበርን የሚያስወገድ ነው ብለዋል ።
ከስራ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ዝነኛ የሆነው የሊንክዲን ማህበራዊ የትስስር ገፅ 4ሺ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የሆኑ የትሰስር ገፁ ተጠቃሚዎች የሊንክዲን አካውንታቸው የሰማያዊ ባጅ እንዲኖረው በቀጥታ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ዘገባው የዘቨርጅ ነው ።