Get Mystery Box with random crypto!

#ግብፅ ግብፅ 40ሺ ሮኬቶችን አምርታ ለሩሲያ ልትልክ አቅዳ እንደነበር ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴ | ebstv worldwide📡☑️

#ግብፅ
ግብፅ 40ሺ ሮኬቶችን አምርታ ለሩሲያ ልትልክ አቅዳ እንደነበር ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ያፈተለከ ነው የተባለው አንድ ሚስጥራዊ መረጃ ይፋ አደረገ፡፡

ዋሽንግተን ፖስት አየሁት ባለው ሚስጥራዊ ሰነድ ግብፅ 40ሺ ሮኬቶችን ለሩስያ ለማምረት ማቀዷ እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ ሮኬቶቹ ሲፈበረኩና ወደ ሩሲያ ሲላኩ በምስጢር እንዲከናወን ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበር ነው የተነገረው፡፡
ይሁንና ግብፅ እቅዷን ለማስፈፀም በተግባር ያሳየችው አፈፃፀም እንደሌለ ነው የተዘገበው፡፡

የግብፅ አንድ ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ምላሽ ካይሮ በሩሲያ - ዩክሬን ጦርነት አንዱን ሀገር ደግፋ ሌላውን ተቃውማ አለመቆሟን ና ለሩሲያ ሮኬቶች ልትልክ አቅዳ ነበር የተባለውም ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።
ከአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስቴር ያፈተለከው ሚስጥራዊ ሰነድ በኢንተርኔት አማካኝነት ተሰራጭቶ በርካቶች መረጃዎቹን እየተቀባበሉት እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

#ሶማሊያ
የመንግስታቱ ድርጅት ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በድርቅ ክፉኛ ለተጐዳችው ሶማሊያ የአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪውን አቀረበ፡፡

በሶማሊያ ጉብኝት ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐሙድ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ በሰብዓዊ ቀውስ እየተፈተነች ላለችው ሶማሊያ የለጋሽ ሀገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተማፅነዋል።
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡

#ኩዌት
የኩዌት የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የበለፀገች ምናባዊ ዜና አንባቢ ይፋ ማድረጉ ትኩረትን ስቧል፡፡

የኩዌት ታይምስ መገናኛ ብዙሃን ንብረት የሆነው የኩዌት የቴሌቪዥን ጣቢያ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገች '' ፌዳ " በመባል የምትጠራ ዜና አንባቢ ጥቅም ላይ ማዋሉ ነው ትኩረትን የሳበው ።
በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የበለፀገችው '' ፊዳ " የምትባለው ዜና አንባቢ አሁን አሁን በመላው ኩዌት ታዋቂ እየሆነች መምጣቷ ተነግሯል፡፡
ዘገባው የሚድል ኢስት አይ ነው፡፡