2023-04-04 18:12:26
መጋቢት 25/2015 ዓ.ም
ፍላጎቱ ላላችሁና ለሚመለከታችሁ የደ/ብ/ዩ መ/ራን በሙሉ
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የመኖሪያ ቤትም ሆነ የቤት መስሪያ ቦታ በከተማው ላሌላቸው የደ/ብ/ዩ መምህራን ዩኒቨርሲቲው በከተማው ካለው ጉልህ የልማት ተሳትፎ አንጻር በልዩ ሁኔታ ፍላጎቱ ያላቸውንና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የዩኒቨርሲቲው መምህራንን በቤት መስሪያ ማህበራት እንዲያደራጅ በዩኒቨርሲቲውም ሆን በማህበሩ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።
በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ለዩኒቨርስቲው ባለው የባለቤትነትና የተቆርቋሪነት ስሜትና ዩኒቨርሲቲው ያለውን የልማት ተሳትፎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለማደራጀት ፍቃደኝነቱን ስላሳየ ፍላጎቱ ያላችሁ እስካሁን ድረስ በስማችሁም ሆነ በትዳር አጋራችሁ ምንም አይነት የመኖሪያ ቤትም ሆነ የቤት መስሪያ ቦታ የሌላችሁ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፊታችን አርብ 29/07/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ባዘጋጀውና በማህበሩ ቴሌግራም ቻናል ሊንኩ በተለቀቀው Google Docs ላይም ሆነ በማህበሩ ጽ/ቤት በአካል በመምጣት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ቁጥሮች ላይ መደወል ይቻላል።
0911-16 35 04
0918-46 93 81
0913-21 68 37
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር
ማሳሰቢያ
1. እንደማንኛውም ነዋሪ በሌላ ፕሮግራም በነዋሪነት ለመደራጀት የምትመርጡ
መምህራን ምርጫው የግላችሁ መሆኑን እንገልጻለን።
2. በት/ት ላይ ያላችሁ መምህራንም የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ።
3. ለግንባታ ወጪ ከባንክ ጋር በማስተሳሰር ብድር የማግኘት እድል ሊኖር ይችላል።
4. ስለ አደረጃጀት ለመወያየት ሚያዚያ 03/2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ
ከመምህራን ጋር አጭር ውይይት ይደረጋል
@debreberhan_university
2.5K viewsedited 15:12