Get Mystery Box with random crypto!

ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph

የቴሌግራም ቻናል አርማ bieteyoseph — ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph
የቴሌግራም ቻናል አርማ bieteyoseph — ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph
የሰርጥ አድራሻ: @bieteyoseph
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 552
የሰርጥ መግለጫ

የተራበች ነፍስ ፣ የተራበ ሀገርና ህዝብ የሃይማኖት አዝመራን የሚሸምትበት ፤ የቅዱሳንን ዳረጎትና ፍርፋሪ የሚቋደስበት ፤ የሕይዎት ክንውኑን በኦርቶዶክሳዊ እሳቤ የሚያነፅርበት ገፅ ነው!
የዚህ ኅብረት አካል ሲሆኑ ፤ ለተቸገሩት የመድረስን እርምጃ ወደ ፊት ይጓዛሉ፥ያስቀጥላሉ።
ለአሁንና ለነገው ትውልድ ፥
ዛሬን በቤተ-ዮሴፍ ማዕድ !
ቤተ-ዮሴፍ
https://t.me/bieteyoseph

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-03 19:35:14 Watch "MK English Album || Proclaim His Name || He Never Left አልተወኝም" on YouTube


235 views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 19:34:51 Watch "MK English Album || Proclaim His Name || The Holy Virgin Mary ማርያም ድንግል" on YouTube


228 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 19:31:31 Watch "MK English Album || Proclaim His Name || St. TekleHaymanot ለተክለሐይማኖት ጻድቅ" on YouTube


245 views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 15:16:35
አቤቱ የልብ ሰው አድርገኝ።
265 views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:14:51 ዘሪ ሊዘራ ወጣ
ማቴ 13፥3
ገበሬ አንተ ፥ ልትዘራ ስትወጣ
ወደ መሬት ልጅህ ፥ ወደ እኔ ስትመጣ
ይህንን እይልኝ
ይህንን ተረዳልኝ
ሁሉም እንደሚያውቀው ፥ እኔ የምገኘው ...
በሁሉ ማለፊያ ፥ በዓብይ መንገድ ዳር ነው።
በዚያውም ላይ ሌላ ምልክት
በጭንጫ እኔነት፥ እሾህ አሜካላ ፥ በብዙው በቅሎበት
በምድር መካከል ፥ ታገኘዋለህኝ ፥ የእኔን መሬትነት።
ጌታዬ ...!
እሾህ አሜካላ ፥ በእኔ ላይ እያለ ፥ በእኔ እየኖረ
መሬት ልቦናዬ ፥ በረድኤትህ ቅፅር ደግሞም ካልታጠረ
ጭንጫ ልቦናዬ ፥ ካልተስተካከለ
መልካም መሬትነት ፥ በእኔ ዘንድ ከሌለ
ፍሬን እንደማልሰጥ ፥ ልቤ ስለሚያውቀው
ይህንን እላለው ...
እጠይቅሃለሁ ፥ እሞግትሃለው
ፍሬ ማፍራትን የምትሻ ፥ ይችን ጉስቁል መሬት
ከመዝራትህ በፊት ፥ አንተው አስተካክላት ፥ አንተው አበጃጃት
እሾሁን ነቃቅለህ
አሜካላውን አቃጥለህ
በጸጋ ጎብኝተህ ፥ በረድኤትህ አጥረህ
ከመንገድ ዳርነት ፣ በፍፁም ታደጋት
ፍሬን የምትሰጥ ፥ መልካም መሬም አርጋት
በከኃሊነትህ ፥ እንደገና ስራት
በፈጣሪነትህ ፥ እንዳዲስ ፍጠራት
ያኔ ዘር ብትዘራ ፥ ቃልህን ብትወረውር ፥ አስተውላለሁ...
ቃልህን ጸንሸ ፥ የመንፈስን ፍሬ ፥ በእውነት እሰጣለሁ።

ያሊያ ግን ...
ጭንጫነቴን ሳታስወግድ ፥ ቅፅርን በእኔ ሳታኖር
አሜካላንም እሾህን ፥ ከእኔ ሳትነቅል
እንደይጠቅመኝ እያወቅህ ፥ ዘርን አትዝራብኝ
ዘሪን በማድከምና ዘርን በማባከን ፥ አታስፈርድብኝ

ደግሞም እውነቱን ልንገርህ
አቋሜ ይሄውልህ !
መሬት ነህ ብለኸኝ
በክብር ፈጥረኸኝ
በጭንጫነቴ ላይ ፥ ዘር ሲበቅል ዐይቼ
ልቤን ሐሴት ሞልቶት ፥ በጣም ተደስቼ
ወዲያውኑ የሚደርቅ
በእሾህ የሚታነቅ
በወፍ የሚለቀም
ለማንም የማይጠቅም
ሲሆን ስለ ማዬት ፥ ...
ራሴን እየወቀስኩ
ፍፁም እየተከዝኩ
ላም አለኝ በሰማይ ፤ እንደስካሁን ያለ ፥ ሕይወት ከምገፋ
ጌታዬ ሰርዘኝ ፥ ከፍጥረትነት መዝገብ ፥ መሬት ልጅህ ልጥፋ
ዮሴፍ ጌትነት
27/10/13 ዓ.ም
304 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:14:17
ዘሪ ሊዘራ ወጣ !
ማቴ 13፥3 ... ይቀጥላል
269 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:24:38
+++ ሰማዕትነት ማለት +++
ዓላዊ ነገስታት ፥ በሰለጠኑበት
የዓለማዊነት እሳቤ ፥ በሚዎደስበት
እግዚአብሔርን መፍራት ፥ ፍፁም በሌለበት
አምልኮ ውዳሴ ፥ ለክብሩ መቀኘት
የመቀደስ ሃሳብ ፥ በጠወለገበት
አሁን በዚህ ሰዓት ...
በጎልያዶች ዛቻ ፥ በፈርዖናዊያን ምክር
በመስቀሉ ዕንቅብ ተደፍቶ ፥ ጣዖት በአዋጅ ሲከበር
ክርስቶስን ያሉ ፥ ሲገፉ ፥ ሲገረፉ
አንገታቸው ሲቀላ ፥ ደምን ከሰውነታቸው ሲያጎርፉ
ታቦት ባህር ሲጣል
ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል
አሁን በዚህ ሰዓት...
ሰማዕትነት ማለት
ምስክርነት ነው ፥ በኑሮ የሚገልጡት
አንድም
በዓላዊያኑ በነገስታቱ ፊት...
እኔ ክርስቲያን ነኝ
ከክርስቶስ ፍቅር ፥ የለም የሚለየኝ
ብሎ መመስከርና ለክብሩ መቀኘት
አንገቴ ይበጠስ ከማዕተቤ በፊት
ስለ ስሙ ልኑር ስለ ስሙ ልሙት
አንድም
ዓላዊ ነገስታት ፥ የስሜት ሕዋሳት
በፍትዎት ማዕበል ፥ ነፍስን ሲያስጨንቋት
ለአይን አምሮትና ፥ ለልብ ክፉ ምኞት ፥ አልገዛም ማለት
በንጹሕ አኗኗር ፥ መመስከር በሕይዎት
አንድም
ጎልያድ በበዛበት በዚህ ክፉ ዘመን
ለወገን ስለ መድረስ ህዝብን ስለማዳን
ተግዳሮትን ስለማራቅ ፥ ለቤቱ ስለመቅናት
መጀገን መታጠቅ ፥ የራስን ወንጭፍ ማንሳት ፥ መሆን እንደ ዳዊት
አንድም
ሀሰት በበዛና ፥ ፍርድ በተገመደለበት
ደካማና ምስኪን አንገት በደፋበት ፥ አሁን በዚህ ሰዓት
ከተገፉትና ከእውነት ጎን መቆም
ሀሰትን መገሰፅ ፥ ሀሰትን መቃወም
ስለ እውነት ዋጋ መክፈል
ስለ እውነት መመስከር
አንድም
መስቀል ቀባሪነት ፥
ጣዖት አክባሪነት
እንዲህ በበዛበት
እውነት እንዲገለጥ ፥ ዓለም እንዲያከብረው
ሰማዕትነት ማለት ፥ እሌኒን መሆን ነው
ሰማዕትነት ማለት
ቆስጠንጢኖስነት
ሰኔ 23/2013 ዓ.ም ዝክረ ሰማዕታት ዘኦሮሚያ
https://t.me/bieteyoseph
375 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:23:19 ሰማዕትነት ማለት

ስለ ስሙ መኖር ፥ ስለ ስሙ መሞት
ይህም ሲተረጎም
ብሞትም ብኖርም
ክርስቶስ ይከብራል በእኔ ስጋና ደም
ለእኔ ነውና ሕይወቴ ክርስቶስ ፥
ሞትም ጥቅም ነው ፥ ወደሱ የሚያደርስ
ስጋዬም እንኳን ቢሆን ፥ ገዝፎ የሚታዬው
የእኔ የምለው የለም ፥ የእርሱው ገንዘብ ነው
የዓይኔ ማዬትና ፥ የጆሮየ መስማት
የእጆቼ መዳሰስ ፥ የአፍንጫዬ ማሽተት
የስሜት ሕዋሳቶቼ ፥ አካሌ በመላ
ምኞት የላቸውም ከክርስቶስ ሌላ
ሰማያዊ መዓዛ ሰማያዊ ውበት
ሰማያዊ ሃገር ሰማያዊ ርስት
ሰማያዌ ተስፋ ሰማያዊ ናፍቆት
የምስጢር ማዕበል ልቤን ማርኮ ወስዶት
የዓለም ውበቷ
መልክ ደምግባቷ
በእኔ ዘንድ ምንም ነው
ስለ ጌታዬ እውቀት ፥ ርሱን እንድመስለው
ረብ ያለው ሁሉ ለእኔ እንደ ጉድፍ ነው።

የሰማዕታት በረከት ይድረሰን ።
አሜን።
ሰኔ 23/2014 ዓ.ም ዝክረ ሰማዕታት ዘኦሮሚያ
https://t.me/bieteyoseph
287 views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:45:08
<<እነርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገቡ እንጅ ቤተክርስቲያን እነርሱ ውስጥ አልገባችም ማለት ነው።
አንተ ውሃ ውስጥ ስትሆን ትዋኛለህ ፤ ውሃው አንተ ውስጥ ሲሆን ግን ትጠጣለህ። የሚዋኝ እንጅ የሚጠጣ ክርስቲያን ጥቂት ነው።
... ሕዝቡ ትንንሽ የሚላቸውን ግፎች አይቶ እንዳላየ ስለሚያልፋቸው ትልቁ ግፍ ሲመጣ መመከት ያቅተዋል።
... እኛ ሀገር ሃብታምነት ሌላ ፕላኔት ውስጥ መኖር ነው። ድኅነት ደግሞ ሌላ ፕላኔት። >>
338 views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:35:14 "የሕይዎት" ና "የስኬት" ትርጉሙ ጠፍቶብናል።

የሰው ልጅ የተፈጠረው በዓላማ ነው። ስለዚህም በተሰጠው የምድር ላይ ቆይታ ለዓላማ ኖሮ በዓላማ ያልፋል።

አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ ሳሉ "ገነትን ያበጃጇት" ዘንድ የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው።
ስለዚህም "ስራ" የሰው ልጆች የመኖር ትርጉም የሚገለጥበት ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጆች የተሰጠ ትዕዛዝና መመርያ ነው።

ለሰው ልጅ መስራት ተፈጥሮአዊ ነው። ስለሆነም እየሰራ ደግሞም ለመስራት ይኖራል።
ለሰራው ስራ እንደ ምስጋናና እና እንደ እውቅና መስጫ የሚሆን በረከት ይሰጠዋል። ይህም የስጋ ብሎም የነፍስ በረከት ነው።
"የስጋ" ቢሉ ፥ ለዕለት ጉርስ ለዓመት ልብስ የሚሆን ዋጋ ያገኝበታል።
"ለነፍስ" ቢሉ በስራው ስላሳየው ትጋት ብፁዕ መባልን ገንዘብ ያደርግብታል።
<<ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው።>> እንዲል የወንጌል ቃል።
ከተፈጠረበት ዓላማ አንፃር
<<መኖሬ ለእኔና ለሌሎች ያለው ሚና ፣ ትርጉምና ፋይዳ ምንድን ነው?>> የሚለው ጥያቄ ፥ የዕለት ከዕለት መልስ የሚያሻው የሰው ልጅ የዘወትር ጥያቄ ሊሆን ይገባል።
ይህም በስራ ይገለጣል።
በኦርቶዶክሳዊ እይታ ስንመለከተው ፥ ስራን የምንሰራበት የመጀመርያው መሰረታዊ ዓላማ ዓለምን ማበጃጀት ነው።
ይህም "ዓለም-ስነፍጥረትን" መልክና ውበት እንዲይዝ ማድረግ ፤ "ዓለም-የሰው ልጅ" ያማረና የተወደደ ሕይዎትን እንዲመራ ማስቻል ነው።
አሁን ላይ ሁላችንም የትርጉም ተፋልሶ አጋጥሞናል። ትልቅ ትውልድ ክፍተት /Generation Gap/ ይስተዋላል።
የመስራታችን ዓላማ ፥ ከስራ መሰረታዊ ዓላማ አፈንግጧል።
ሕይዎትን የማበጃጀት ትርጉማችን ተንሽዋሯል።

የእኛና የሌሎችን ሕይዎት የሚያበጃጀው ስራ ሳይሆን ገንዘብ መሆኑን ወድ0 ማመን ደርሰናል።
<<ብዙ ብር የሚያስገኝ ስራ ?>> የእኔና የሌሎችን ሕይዎት የሚያበጃጅ ፥ የማ/ሰብን ችግር የሚቀርፍ ስራ ምንድን ነው ብለን አንጠይቅም። ማሰብም አንፈልግም።

የስኬታችን መመዘኛም ፥ በተሰጠን ዕድሜ ለሌሎች የሰጠነው አገልግሎትና ያበጃጀነው ሕይዎት ሳይሆን ፥ ያገኘነው የቁስና የገንዘብ መጠን ሆኗል።
ስለዚህም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወይም የሰዎች አገልጋይ ሳይሆን ገንዘብን የምናገለግል ሁነናል።
"የሰው ልጅ ሰውን ሊያገለግል እንጅ እንዲያገለግሉት አልመጣም" ያለንን ጌታ የሚያስመስለንን ስራ ገንዘብ አላደረግንም።

ወንጌል "ሰው ለሁለት ጌታ አይገዛም" ብሎናል። በስራችን የእግዚአብሔርን አሳብ ወይም የሰውን ልጅ ለማገልገል ካልተጋን ፤ ገንዘብን የምናገለግል ስለመሆናችን ለጌታ አልተገዛንም ማለት ነው።
በሁለት ልብ የምናነክስ ሆነናል።
ስለዚህም ደስታ የመንፈስ ፍሬ ነው ። እውነተኛ ደስታን በስራችን ውስጥ ልናገኘው አንችልም።
ብዙ የሰራን ፣ ብዙ የደከምን ቢመስለንም ያገለገልነው ገንዘብን ብሎም የስጋ ፈቃዳችን እንጅ ፥ የእግዚአብርን አሳብ አይደለምና ደስታ ይርቀናል።
እናስተውል ! ራሳችን እንፈትሽ!
• ስንማር ፥ በእኔ ዙርያ ያሉትን ሕይዎት ለማበጃጀት ፣ ችግራቸውን ለመፍታት ልማረው የሚገባኝ እውቀት ፣ ልይዘው የሚገባኝ ጥበብ ምንድን ነው ብለን ዐቅደን እናውቅ ይሆን?
• ያለኝን እውቀትና ጉልበት ተጠቅሜ ልፈታው የምችለው የማ/ሰብ ችግር የትኛው ነው ብለን አስበንስ?
• እየሰራሁት ባለሁት ስራ የተስተካከለ የሌሎች ሕይዎት ፣ የተፈታ ችግር ምንድን ነው? የእኔ ጨውነት ፣ ብርሃንነት ፣ እርሾነት የት አለ?
ብለን ስራችንን መዝነናል?

እንዲያ ቢሆን ኖሮ ...
• ስራችን የማስመሰል አይሆንም ነበር።
• ስራችን አድካሚ ቢሆንም እንኳ ፥ በድካማችን ደስ የሚለን በሆንን የነበር።
• አንዳችን የሌላችን ሕይዎት የምናበጃጅ ስለመሆናችን ፤ በእኛ ዘንድ ፍቅር በዝቶ በተትረፈረፈ የነበር።
•የዕለት ስራችን በረከተ ስጋ ወነፍስ የሚያስገኝልን በሆነልን የነበር።

እንዲያ ግን አልሆነም...
በዙርያችን ያሉትን ሰዎች ችግር ከማየት አንጀምርም ። ጥሩ ገንዘብ የሚያገኙ ሰዎች ፥ እየሰሩ ስላሉት ነገር እንጅ።

ከማ/ሰቡ የምናገኘውን ጥቅም እንጅ ፤ ለማ/ሰብ የምናስገኘውን ጥቅም ፥ የምንጨምረውን ፋይዳ የምናመጣውን መፍትሔ ቅድሚያ ሰጥተን ስራ አንጀምርም።
ስለዚህም ስራችን ሌሎችን ከድካማቸው የሚያሳርፍ አይደለም። ገንዘብ እንጅ ርካታ ከኛ ርቊል። በስራችን የሌሎችን እንባ ለማበስ አልታደልንም።

ነጋዴው ፥ ማ/ሰቡ የጎሰለውና። ያጣው እኔ የምጨምርለት ነገር ምንድን ነው በሚል ስሌት ስራውን አይጀምርም።
የመኪና አሽከርካሪው ፥ የተጓዦችን ችግር መፍታትን ተቀዳሚ ስሌት አያደርግም።
መ/ሩ ፥ የተማሪዎቹን አዕምሮ መቅረፁ ተጨማሪ እንጅ ቀዳሚ ገዳዩ አልሆነም።
ሀኪሙ ፥ የታመመ የሰው ልጅ - በመዳኑ ውስጥ ያለው ሚና ነፍሱን የሚሰጥለት ተቀዳሚ ጉዳይ ሲሆን አይታይም።
መሐንዲሱ ፥ የሚፈታው የመንገድ ፣ የውሃ ፣ የመብራት ፣ ... ችግሮች ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ ጉዳዩ ናቸው።
ዳኛው ፥ "ድሃ እንዳይበደል ፣ ፍርድ እንዳይጓደል" የሚል የስራ መርሁን የሚጋርዱበት ፥ ሌሎች ጉዳዮች አሉት።
ባለስልጣኑ ፥ ሌሎችን ሊያገለግልበት የተሰጠውን ስልጣን - ሌሎች እንዲያገለግሉት የመጎሰሚያ በትር ያደርገዋል።
ፖሊሱ ፣ ... ሌላውም ሌላውም
አሁን አሁን ይህ ጉዳይ ወደ ሃይማኖት ተቋማትም ተጋብቷል።
ይህም ለማ/ሰቡ እንድናበረክት ከያዝነው ኃላፊነት /የስራ ድርሻ ይልቅ/ ፥ እሱን ተጠቅመን የምናገኘው ገንዘብ ተቀዳሚ ዓላማ ሆኗል።
ይልቁንም ደክምን ከምናገኘው ገንዘብም ባሻገር የተመደብንበትን የስራ መደብ ተጠቅመን ፥ የሌሎችን የድካም ዋጋ ያላግባብ የምናግበሰብስበትን መዋቅራዊ አሰራር ወደንና ለምደን ተቀብለነዋል።

በአካባቢያችን ነግዶ ያተረፈ ስናይ ፤ ከሱ አጠገብ ተመሳሳይ የንግድ ስራ ይዘን ቁጭ እንላለን። ሌላም ሌላም የዚህ ነፀብራቆች ናቸው።

ያልሰራንበትን ስናገኝ ጥቂት ለአዕምሮአችን አይከብደንም። እጅ ስመን እንቀበላለን።
ለመኖር የምንሰራ እንጅ ፤ ለመስራት የምንኖር አይደለንም።
ስለማይቻል እንጅ ቁጭ ብለን ፥ መብላት ብንችል ኖሮ ወይም ምግብና ልብስ መሰረታዊ ፍላጎቶች ባያስፈልጉን ኖሮ ስራ ለምኔ የምንል ሰዎች በሆን የነበር።
ብቻ ... ስንቱ ...
ምን ይሻላል ትላላችሁ ... ?
20/10/2014 ዓ.ም
ዮሴፍ ጌትነት
345 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ