Get Mystery Box with random crypto!

ሰማዕትነት ማለት ስለ ስሙ መኖር ፥ ስለ ስሙ መሞት ይህም ሲተረጎም ብሞትም ብኖርም ክርስቶስ | ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph

ሰማዕትነት ማለት

ስለ ስሙ መኖር ፥ ስለ ስሙ መሞት
ይህም ሲተረጎም
ብሞትም ብኖርም
ክርስቶስ ይከብራል በእኔ ስጋና ደም
ለእኔ ነውና ሕይወቴ ክርስቶስ ፥
ሞትም ጥቅም ነው ፥ ወደሱ የሚያደርስ
ስጋዬም እንኳን ቢሆን ፥ ገዝፎ የሚታዬው
የእኔ የምለው የለም ፥ የእርሱው ገንዘብ ነው
የዓይኔ ማዬትና ፥ የጆሮየ መስማት
የእጆቼ መዳሰስ ፥ የአፍንጫዬ ማሽተት
የስሜት ሕዋሳቶቼ ፥ አካሌ በመላ
ምኞት የላቸውም ከክርስቶስ ሌላ
ሰማያዊ መዓዛ ሰማያዊ ውበት
ሰማያዊ ሃገር ሰማያዊ ርስት
ሰማያዌ ተስፋ ሰማያዊ ናፍቆት
የምስጢር ማዕበል ልቤን ማርኮ ወስዶት
የዓለም ውበቷ
መልክ ደምግባቷ
በእኔ ዘንድ ምንም ነው
ስለ ጌታዬ እውቀት ፥ ርሱን እንድመስለው
ረብ ያለው ሁሉ ለእኔ እንደ ጉድፍ ነው።

የሰማዕታት በረከት ይድረሰን ።
አሜን።
ሰኔ 23/2014 ዓ.ም ዝክረ ሰማዕታት ዘኦሮሚያ
https://t.me/bieteyoseph