Get Mystery Box with random crypto!

All Art 2

የቴሌግራም ቻናል አርማ allartlove — All Art 2 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ allartlove — All Art 2
የሰርጥ አድራሻ: @allartlove
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 126
የሰርጥ መግለጫ

-ግጥሞችን ~አዝናኝ ወጎችን
-አስቂኝ ቀልዶች. ~ቅኔዎች
- አስደሳች ታሪክዎች ~አፈታሪክ
-አስደናቂ Video
- ጠቅላላ እውቀት
✍✍🏾አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል።
ስለመረጡ እናመሰግናለን
JOIN & SHARE @AllArtLove

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-28 23:29:04 ትዝታ

ሁሉምይወጣል ይወርዳ በትዝታ ዳገት
ዉስጡን ያደማዋል ሁልጊዜ በስለት
እኔም እንደዛዉ ነኝ የትዝታ ሚዜ
ወደኋላ የምመለስ በሀሳብ በትካዜ
ሄዳለች እኮ የለችም ከጎኔ
ግን አጠገቤ ያለች ይመስለኛል እኔ
ሁል ጊዜ ሲነጋ እሷን አስባለው
ቀኑን ሙሉ በምናብ ሳያት እዉላለዉ
ሁልጊዜ ሲመሽ እሷን አስባለው
አንዳንዴም አንዳንዴም በህልሜ አያታለዉ
ደሞኮ የማያት በጣም ስትስቅ ነው
ብቻዬን ሰቃለው ሳቋን እያሰብኩት
ዉስጤ እየደማ በትዝታ ስለት
ከዛም ብርሀን ፍጥነት በአንድ አፍታ
ዉስጤን ወረረኝ የዛች ልጅ ትዝታ
ሳቄን እረሳሁት በከባዱ አለቀስኩ
አጠገቤ አለመኖሯን መሄዷን እያሰብኩ
አምላኬን እላለሁ ለምን እሷን ብቻ
አንድ መሆን ነበር ይላሉ ጋብቻ
እባክህ አምላኬ ወደ እሷ ውሰደኝ
ወይም ትዝታዬን ወደ እኔ አምጣልኝ
470 viewsK̃ãL̃, 20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 18:30:29
በህይወት ውስጥ ምን ያስፈልጋል????
Anonymous Quiz
71%
ሰው
29%
ብር
21 voters122 viewsK̃ãL̃, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 23:55:06 ካልመጣህ¿¿¿¿¿¿¿

ባትመጣም ቅጠረኝ
ሺ ጊዜ ልገተር
ፀሀይ ቆማ ትቅር
ብርሀንም ይፈር
ጨለማ ያሸንፍ

የሰዉ ልጅ ከርታታ
እንደቆመ ይቅር
አንተ 'ስክትመጣ
የፈካዉ ይገርጣ

ግሳንግሳም አለም
የምትመካበት ቴክኖሎጂም ይክተም

ብቻ አንተ እስክትመጣ
ደርቆ መቅረት ይሁን የዚች ዓለም እጣ።

ብልህ ደስ ባለኝ
ጅል ሆኖ ባስቀረኝ

የኔ ተናፋቂ................

አንተ ብትመጣም
አንተ ባትመጣም
ደግሞ ብትቀርም
እኔ እንደዉ ለሴኮንድ አንተን አልጠብቅም።

ስለ ፍቅር ብለዉ የቆሙ አዉቃለሁ
ባትመጪም ቅጠሪኝ ሲሉም ሰምቻለሁ
ደግሞም ሲጠብቁ በአይኔ አይቻለሁ

ከዚ ሁሉ መሀል እኔ የተረዳሁት
አፍቃሪዉን ሳይሆን አጠባበቁን ነዉ እነሱ የወደዱት።

አረ እንደዉም ዉዴ..............

በመጠበቅ ብዛት ስሙ የገነነዉ
እሷኑ ቢያሳዩት
እየጠበቃት ነዉ።

ታዲያ ለምን ብዬ
ብትመጣም ባትመጣም ለምረሳህ ነገር
ሴኮንድ አልጠብቅህ ጥቅር ብለህ ብትቀር።

108 viewsK̃ãL̃, 20:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 23:52:50 አንቺ ከሄድሽ ወዲ
.
.
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ
ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ
እማላገኝሽን
እማላገኝሽን
አንቺን አምጣት አለኝ
እሷን አምጣት አለኝ
ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ
እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ

አንቺ ከሄድሽ ወዲህ
መሰለኝ መቃብር
ያለሁበት ሰፈር
ዘልዬ ቦርቄ
ያደኩበት መንደር

ደሞም ባከባቢው
የሚወጣው ድምፀት
የሚሰማው ጩኸት
መሰለኝ የሲኦል
ጫጫታ'ና ሁካታ፥
የአጋንንት ፉጨት
የሐጣን ዋይዋይታ፥
የሐጥአን እሪታ...

እንዲም አስባለሁ
ሰፈርተኛው ሁሉ
ሞልቶለት ሲዘክር
ይመስለኛል የኔ
የአርባዬ ተስካር
የሰማንያ ተስካር
ሙት አመቴን ማውሻ
እኔን ማስታወሻ
ደግሶ ማልቀሻ...

አንቺ ከሄድሽ ወዲ
አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ
ሁሉ በኔ አየለ
ህሊናዬ ዛለ
ዋለለ ቆሰለ
መላው ሰውነቴም
ነደደ ከሰለ
ከሰለ
.
.
እንደው ባጠቃላይ
አንቺ ከሄድሽ ወዲ

ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ
አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!!
82 viewsK̃ãL̃, 20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 23:52:49 አንቺ ከሄድሽ ወዲ
.
.
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ
ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ
እማላገኝሽን
እማላገኝሽን
አንቺን አምጣት አለኝ
እሷን አምጣት አለኝ
ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ
እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ

አንቺ ከሄድሽ ወዲህ
መሰለኝ መቃብር
ያለሁበት ሰፈር
ዘልዬ ቦርቄ
ያደኩበት መንደር

ደሞም ባከባቢው
የሚወጣው ድምፀት
የሚሰማው ጩኸት
መሰለኝ የሲኦል
ጫጫታ'ና ሁካታ፥
የአጋንንት ፉጨት
የሐጣን ዋይዋይታ፥
የሐጥአን እሪታ...

እንዲም አስባለሁ
ሰፈርተኛው ሁሉ
ሞልቶለት ሲዘክር
ይመስለኛል የኔ
የአርባዬ ተስካር
የሰማንያ ተስካር
ሙት አመቴን ማውሻ
እኔን ማስታወሻ
ደግሶ ማልቀሻ...

አንቺ ከሄድሽ ወዲ
አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ
ሁሉ በኔ አየለ
ህሊናዬ ዛለ
ዋለለ ቆሰለ
መላው ሰውነቴም
ነደደ ከሰለ
ከሰለ
.
.
እንደው ባጠቃላይ
አንቺ ከሄድሽ ወዲ

ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ
አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!!
69 viewsK̃ãL̃, 20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 20:58:28
በህይወት ምን ያስፈልጋል?????
Anonymous Poll
67%
ፍቅር
33%
ብር
6 voters66 viewsK̃ãL̃, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 12:26:28 #አድዋ 1888-2014
#126

.....አንድ ቀን ንጉሥ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህ አዋጅ ሀገር ሊቀማ የመጣ ወራሪ እንደፍልፈል ምድራችንን እየሰረሰረ አድብ ቢባል አልሰማ ያለ ነው የሚል ነበር፡፡
የንጉሡን ኣዋጅ ሀገር ሁሉ ሰማ፡፡ ያኔውኑ የሸዋ ሰው ጥቅምት ሲጋመስ ወረኢሉ ገባ፡፡ ያኔ በኢትዮጵያ ምድር የሆነው የአባቶቻችን ገድል እንዲህ ነው፡፡ ከጠረፍ ሀገር ለሚነሱ አባቶቻችን የደዴሳ ወንዝ ሙላት ስጋት አልነበረም፡፡ ከበርሃ ለሚመጡ አባቶቻችን የጥምና የሀሩር ጉልበት ፈተና አልነበረም፡፡
እባቶቻችን እሾህና አሜኬላን ረግጠው፣ በባዶ እግር ሙሉ ሀገር ሊያስረክቡን መንገድ ዠመሩ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ እንዲኽ ሆነ፡፡
የንጉሠ ነገሥታችንን ጥሪ የሰማው ሠራዊት ብዙ ነበር፡፡ ክተት ብሎ የተነሳው ሠራዊት ከጉልበቱ ይልቅ ፈጣሪውን የታመነ ኾነ፡፡ ግቤ ሸለቆን በዱአ ተከዜን በጸሎት የተሻገረው ሠራዊት ለሀገሩ ፍቅር ቁጥሩ ለአብረሃም እንደተገባለት ቃል ኪዳን ከምድር አሸዋ በዝቶ ወደ ስሜን የሚፈስ የሰው ጎርፍ ሆነ፡፡
አባቶቻችን ለንጉሣቸው ቃል ታመኑ፡፡ ብዙቋንቋ፤ በምልክት የሚግባባ፡ በመንፈስ የሚናበብ አንድ ህዝብ ሆነ፡፡ ጠላት እንደ ሰናዖር ሰዎች ኣንዱ ከሌላው ቃሉ ተደበላልቋል ብሎ ሲል በኣንድ ድምጽ በአንድ ቃል ኢትዮጵያ ሲባሉ አቤት ብለው የወጡት ኣባቶቻችን ታላቅ ገድል ይኽ ነው፡፡
በየካቲት ጊዮርጊስ ሌሊት አስራ አንድ ሰዓት የጠላት ጦር ተኩስ ኣሰማ፡፡  የትግራይ ጦር ብጽኑ ተዋጋ፡፡ ይህ ጦርነት በአድዋ ተራሮች ግርጌ ነበር፡፡
ብዙ ተጋድሎ ተደረገ፡፡ አባቶች ለሀገር ክብር ተዋደቁ፡፡ ከወገን ጣር ይልቅ በርታ የሚለውን አዝማሪ መሰንቆና ዜማ የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ወታደር ብዙ ነበር፡፡ ሞት ከአንድ ሽክና ጠላ ቀለለች፡፡ ለሀገር መሞት ትንሳዔ ሆነ፡፡ ከየት ነህ? ያለመባባል ከአንድ ኢትዮጵያ አንድ ኢትዮጵያን ብሎ የተሰለፈው የንጉሠ ነገሥት ጦር ከካሌብ የናግራን ጦርነት በጀመረው የቀደሙት አያቶቹ ክብር ለሀገር መፋለምን አሳየ፡፡
አስቀድሞ በዶጋሊ፣ በጉርዓና በጉንደት እንደሆነው ያለ ለሀገር የተከፈለ መስዋዕትነት መካን ያልሆነች ምድር እንዳለችን አሳመነ፡ይኼ እንደ ኢዛና ጦርነት በድንጋይ የታተመ የድል ታሪክ አልነበረም፡፡ ብራና ፀሐፊዎችም ሞላውን አላስቀሩትም፡፡ ይልቁንስ ሰማይና ምድር ለነጻነት የተከፈለን የጥቁር ህዝብ ተጋድሎ ተመለከቱ።
በአድዋ ተራሮች የኾነው፤ የእኛ ኢትዮጵያውያን ኩራት ብቻ አይደለም፡፡ ጥቁር ሁሉ ይኮራ ዘንድ የተፈጸመ የአያቶቻችን ገድል ነው፡፡ የአድዋ ተራሮች ከዳሞታ እስከ ጉጌ፣ ከዳቲ ወለል እስከ ካራ ማራ፣ ከበላያ እስከ ሙሳ ዓሊ፣ ተራሮቻችን ሁሉ የገድል ሰሌዳ ሆነው የአባቶቻችን ገድል አትመውታል፡፡

የአባቶቻችን ገድል እንዲህ ነው፡፡ ለሀገር በአንድነት ተጋድለዋል፡፡ ሞት በፊታቸው ሸሽቷል፡፡ በመሞት ህይወት ሰጥተውናል፡፡ እንደ ዛሬው ያይደለ፤ አብሮ መብላት ከባድ ሳይሆን፤ አብሮ መሞት ቀላል ሆኖ የድል ቀለም ምሳሌ አድርገውናል፡፡
የአባቶቻችን ገድል በእድል ሳይሆን በሞት የተጻፈ ነው፡፡ የአባቶቻችን ድል ለቂም ሳይሆን ለነጻነት በተከፈለ መስዋዕትነት የተገኘ ነው፡፡

#ምንጭ፦ #ሀገሬን መፅሐፍ
#በተጓዡ_ጋዜጠኛ_ሄኖክ_ስዩም

#የካሌብ_ጽሑፎች
@AllArtLove
@AllArtLove
@AllArtLove
103 viewsK̃ãL̃, 09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 12:24:50 ፈረስ ሲያስገመግም፣ጦር ጎራዴው ሲፋጅ ፣ተዘከር አድዋ
ሰው በነጻ ሊኖር ሰው እየተሰዋ!

አድዋ ትናንት ነው ፣ ዛሬ ነው ፣ነገ ነው
የእድሜ ዘመን ጸጋ ከአያት የወረስነው

አድዋ ታሪክ ነው አድዋ ተራራ
ባንድ የዘመተበት ሰው ከፅላት ጋራ!

አድዋ "እምነት ነው" የሰማዕት ገድል
ስጋ ብቻ አይደለም መንፈስም ሰው ጥሏል!

አድዋ "ሸማ ነው" ጠቢብ ያሳመረው
ክፉ የማይፍቀው ዘመን ያላስረጀው!

አድዋ ኩራት ነው ሰው የመሆን ክብር
በጥቁር ተሰብሯል ነጭ የገራው ቀንበር!

አድዋ ጸሀይነው ሰው ያነጸው ጮራ
ከሮም ብርሀን ነጥቆ ለጦብያ ያበራ!

አድዋ "በትር ነው" ጠላት የሞተበት
"አልሞት ባይ ተጋዳይ" ድል የከጀለበት!

አድዋ "ቅርስ ነው" አድዋ ስንክሳር
ለኛ ጆሮ ሀሴት ለዚያ ጎራ ሀሳር!

ይናገር ምኒሊክ ይናገር ይመስክር
እምነትና ግዛት እንዴት እንደነበር!!!

ክብር በዓድዋ ተራራ በባዶእግራቸው በጦርና ጎራዴ ዘመናዊ መሳርያን ከታጠቀ ወራሪ ጋር ታግለው ዛሬ በየ ፊናችን "አድዋ አድዋ..." እያልን እንድንዘምር ዋጋ ለከፈሉልን ለኒያ ጽኑና ጀግኖች አባቶቻችን ይሁን!!!

እንኳን ለ 126ኛው የጥቁር የነጻነት ቀን አደረሳችሁ!!!

መልካም የዓድዋ ድል!

(ታደሰ ደምሴ)

@AllArtLove
@AllArtLove
@AllArtLove
82 viewsK̃ãL̃, 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 09:37:45 #የሊስትሮ_እቃዬ
(በቴዲ አፍሮ)

ርሀቤ ቢከሰኝ ~ ባዶ ሆዴን አይቶ
አፌ መሰከረ ~ ችሎት ላይ አዛግቶ
በህይወት ፍርድ ቤት
የተሾሙት ዳኛ ~ መፃፉን ሲገልፁ
ያልሰራ አይብላ ~ ይል ነበር አንቀፁ
ይህንን ስትሰማ
ፈጥና መጣችና ~ ሆና ጠበቃዬ
ከፍርድ አዳነችኝ ~ የሊስትሮ እቃዬ
እኔም እሱዋን ይዤ
አንገቴን ለስራ ~ ጎንበስ እንዳረኩት
ችግሬን በብሩሽ ~ ሲጠረግ አየሁት
የኩራቴን በትር
ወርውሬ ስጥለው ~ ከጄ ላይ ወደዛ
እንኳን የሰው ጫማ ~ የኔም ፊቴ ወዛ
ካመታት ቀጠሮ
ከጊዜ በኃላ ~ የዋለው ችሎት
ጥረቴን አየና ~ ቢፈርድልኝ ሀብት
ከትቢያ ተነስተው ~ እንዲሉ ከማማ
እኔም በተራዬ
ከላይ ተቀምጬ ~ አስጠረኩኝ ጫማ
እንግዲህ አዝናለው
ባለውለታዬ ~ ክብሬ ነሽ እያልኩዋት
ከታች ያነሳችኝ
የሊስትሮ እቃየን ~ ከላይ እረገጥኳት
እንግዲህ አዝናለሁ
ውድዋ…………… የሊስትሮ ዕቃዬ
ምንም እንኩዋን ~ ብትሆኝ ባለውለታዬ
በጫማ ስረግጥሽ ~ አይክፋሽ ግድ የለም
ባታውቂው ነው እንጂ
ለዋለላት ሁሉ ~ እንደዚህ ናት አለም
~||~

ከ ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro)

@AllArtLove
@AllArtLove
@AllArtLove
78 viewsK̃ãL̃, 06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 08:56:18 ሰላም ምርጦቼ እንደምን ቆያቹሁን

አንዲት ኮረዳ ወጣት ከዛ ማዶ ውሃ እየቀዳች በርቀት
የተመለከታት አንድ ወንድ አያት ጠጋ አላትና እስኪ
ንገሪኝ?''አላት!! #የሴቶች_ተንኮል_ምን_ያህል_ነው? ሲል ጠየቃት

እሷም በከፍተኛ ድምፅ ጩህት አሰማች... ልጁም ደነገጠና ምን
ሆንሽ? በማለት ጠየቃት እሷም እንድህ አለችው... ሊደፍረኝ
ነው ብየ ለሰዎች እነግራለሁ። ሰዎቹም ይገሉሃል አለችው።
እሱም ኢንድህ አለ .. ጥሩና አስተዋይ መስለሽኝ ግራ ያጋባኝን
ነገር ልጠይቅሽ እንጅ ባንች ላይ ክፉ ነገር መስራት አስቤ
አልነበረም አላት እናም ሰዎቹ ከዛ ማዶ ተንደርድረው መጡ....
#በባልዲ ውስጥ የነበረውን ውሃ በሯሷ ላይ
ለቀቀችው።...

ጩህቷን የሰሙት ሰዎችም ተንደርድረው ሲመጡ
ምን ሆነሽ ነው?ሲሉ ጥይቋት ውሃ ውስጥ ገብቼ ይሄ ልጅ ነው
ያወጣኝ በማለት ለሰዎቹ መልስ ስጠቻቸው
ሰዎቹም ልጁን አመሰገኑትና ወደቤታቸው ተመለሱ....ልጁም
ግራ በመጋባት ለምንድን ነው ይህን ያደረግሽው ሲል
ጠየቃት.
.
.
.... አየህ? ሴት ልጅ ተንኮሏ ይህ ነው። ሴት ልጅ
ማስገደልም ትችላለች ማስመስገንም ትችላለች አለችው።
እና ሴት ልጅ ስታከብራት ታከብርሃለች.. ስትንቃት ደግሞ
ታስገድልሃለች ሴትን ልጅ አክብራት ሴትን ልጅ ለማክበር
ምክንያት አያስፈልግም ምክንያቱም ከፈጣሪ ለአዳም ልዩ ስጦታ
የተሰጠች ሴት ነች እና.......፡ ሰላም ዋሉልኝ

Semir

@AllArtLove
@AllArtLove
@AllArtLove
73 viewsK̃ãL̃, 05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ