Get Mystery Box with random crypto!

አንቺ ከሄድሽ ወዲ . . አንቺ ከሄድሽ ወዲ ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እ | All Art 2

አንቺ ከሄድሽ ወዲ
.
.
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ
ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ
እማላገኝሽን
እማላገኝሽን
አንቺን አምጣት አለኝ
እሷን አምጣት አለኝ
ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ
እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ

አንቺ ከሄድሽ ወዲህ
መሰለኝ መቃብር
ያለሁበት ሰፈር
ዘልዬ ቦርቄ
ያደኩበት መንደር

ደሞም ባከባቢው
የሚወጣው ድምፀት
የሚሰማው ጩኸት
መሰለኝ የሲኦል
ጫጫታ'ና ሁካታ፥
የአጋንንት ፉጨት
የሐጣን ዋይዋይታ፥
የሐጥአን እሪታ...

እንዲም አስባለሁ
ሰፈርተኛው ሁሉ
ሞልቶለት ሲዘክር
ይመስለኛል የኔ
የአርባዬ ተስካር
የሰማንያ ተስካር
ሙት አመቴን ማውሻ
እኔን ማስታወሻ
ደግሶ ማልቀሻ...

አንቺ ከሄድሽ ወዲ
አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ
ሁሉ በኔ አየለ
ህሊናዬ ዛለ
ዋለለ ቆሰለ
መላው ሰውነቴም
ነደደ ከሰለ
ከሰለ
.
.
እንደው ባጠቃላይ
አንቺ ከሄድሽ ወዲ

ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ
አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!!