Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ምርጦቼ እንደምን ቆያቹሁን አንዲት ኮረዳ ወጣት ከዛ ማዶ ውሃ እየቀዳች በርቀት የተ | All Art 2

ሰላም ምርጦቼ እንደምን ቆያቹሁን

አንዲት ኮረዳ ወጣት ከዛ ማዶ ውሃ እየቀዳች በርቀት
የተመለከታት አንድ ወንድ አያት ጠጋ አላትና እስኪ
ንገሪኝ?''አላት!! #የሴቶች_ተንኮል_ምን_ያህል_ነው? ሲል ጠየቃት

እሷም በከፍተኛ ድምፅ ጩህት አሰማች... ልጁም ደነገጠና ምን
ሆንሽ? በማለት ጠየቃት እሷም እንድህ አለችው... ሊደፍረኝ
ነው ብየ ለሰዎች እነግራለሁ። ሰዎቹም ይገሉሃል አለችው።
እሱም ኢንድህ አለ .. ጥሩና አስተዋይ መስለሽኝ ግራ ያጋባኝን
ነገር ልጠይቅሽ እንጅ ባንች ላይ ክፉ ነገር መስራት አስቤ
አልነበረም አላት እናም ሰዎቹ ከዛ ማዶ ተንደርድረው መጡ....
#በባልዲ ውስጥ የነበረውን ውሃ በሯሷ ላይ
ለቀቀችው።...

ጩህቷን የሰሙት ሰዎችም ተንደርድረው ሲመጡ
ምን ሆነሽ ነው?ሲሉ ጥይቋት ውሃ ውስጥ ገብቼ ይሄ ልጅ ነው
ያወጣኝ በማለት ለሰዎቹ መልስ ስጠቻቸው
ሰዎቹም ልጁን አመሰገኑትና ወደቤታቸው ተመለሱ....ልጁም
ግራ በመጋባት ለምንድን ነው ይህን ያደረግሽው ሲል
ጠየቃት.
.
.
.... አየህ? ሴት ልጅ ተንኮሏ ይህ ነው። ሴት ልጅ
ማስገደልም ትችላለች ማስመስገንም ትችላለች አለችው።
እና ሴት ልጅ ስታከብራት ታከብርሃለች.. ስትንቃት ደግሞ
ታስገድልሃለች ሴትን ልጅ አክብራት ሴትን ልጅ ለማክበር
ምክንያት አያስፈልግም ምክንያቱም ከፈጣሪ ለአዳም ልዩ ስጦታ
የተሰጠች ሴት ነች እና.......፡ ሰላም ዋሉልኝ

Semir

@AllArtLove
@AllArtLove
@AllArtLove