Get Mystery Box with random crypto!

AACRA

የቴሌግራም ቻናል አርማ addisroads — AACRA A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addisroads — AACRA
የሰርጥ አድራሻ: @addisroads
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.84K
የሰርጥ መግለጫ

Addis Ababa City Roads Authority (AACRA) is a government organization under the Addis Ababa City Adminstration. It was established on March 1998 with the aim of realizing sustainable road infrastructure and creating interchangeable road transport to A.A.

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 18:20:39
1.4K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:20:33 ከአየር ጤና -ወለቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአየር ጤና - ወለቴ ሱቅ- አለም ገና አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮንትራት ውል በዛሬው ዕለት ፈርሟል፡፡
ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 5.6 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይርጋዓለም ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት በ2 ዓመት ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ የኮንትራት ውል ፈርሟል፡፡ ጎንድዋና ኢንጂነሪንግ ደግሞ የማማከርና የቁጥጥሩን ተግባር የሚያከናውን ይሆናል፡፡
ነባሩ የአየር ጤና - ወለቴ መንገድ ተገቢውን የትራፊክ ፋሲሊቲዎችን ያላካተተ እና ወጥ የሆነ ስፋት የሌለው በመሆኑ አሁን ላይ እያደገ የመጣውን ከፍተኛ የትራፊክ መጠን ለማስተናገድ የማይችል ጠባብ መንገድ ነው፡፡
በዚህ ውል መሠረት የሚገነባው አዲሱ መንገድ ፈጣን የአውቶብስ መተላለፊያ መስመርን አካቶ የሚገነባ ከመሆኑም በተጨማሪ 4.5 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ እና ዘመናዊ የመንገድ ፋሲሊቲዎች እንዲኖረው ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et
1.4K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:19:39
1.2K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:19:15 ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የግንባታ ወጪ ያላቸው የሦስት መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ውል ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የግንባታ ወጪ ያላቸው ሦስት የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን የውል ፊርማ ስነስርዓት አከናውኗል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ የግንባታ ወጪ በከተማ አስተዳደሩ እና ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚሸፈን ሲሆን በአጠቃላይ 10 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ15 እስከ 30 ሜትር የጎን ስፋት የሚኖራቸው ይሆናል፡፡

ውል ከተፈረመላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል በዓይነቱ ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን Intelligent Transport System (ITS) ያካተተ ዲዛይን የተሰራለትና የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን ያግዛል ተብሎ የሚታመነው ከአፍሪካ ጎዳና - ኤድናሞል አደባባይ - 22 ማዞሪያ - እንግሊዝ ኢምባሲ የአስፋልት መንገድ አንዱ ሲሆን የግንባታ ስራው በቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሚከናወን ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የአየር ጤና - ወለቴ ሱቅ - አለም ገና አደባባይ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲሆን የግንባታ ስራው ይርጋለም ኮንስትራክሽን በተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ሦስተኛው እና የመጨረሻው ደግሞ የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ሲሆን ብርጂ ኮንስትራክሽን በተባለ አገር በቀል የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ስራውን የሚያከናውነው ይሆናል፡፡ ይህ የድልድይ ግንባታ 61.2 ሜትር ርዝመትና 25 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et
1.3K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:46:49
879 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:46:17 በጂ.ፒ.ኤስ መረጃ አሰባሰብ ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓም፡-
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የመንገድ ግንባታ የመስክ መረጃ አያያዝና አሰባሰብ ሥራን ለማዘመን የሚያስችል የእጅ ጂ.ፒ.ኤስ አጠቃቀም ስልጠና ለሰርቬይንግ ባለሙያዎች ተሰጠ፡፡

የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበዜ ሱሌማን እንደገለፁት ስልጠናው በዋናነት በቅርቡ በጨረታ ተገዝተው የገቡ የእጅ ጂፒኤሶችን አጠቃቀም የተመለከተ እንደሆነና በመስክ መረጃ አሰባሰብ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የተሰጠ የተግባር ልምምድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሥልጠናው በመንገድ ቅየሳና ዳታ አሰባሰብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ባገኙት የተግባር ልምምድ በመታገዝ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመረጃ አያያዝ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው ጨምረው ገልፀዋል።

ስልጠናው በተለይም የዳታ ቤዝ አስተዳደር፣ የዲዛይን እና የመንገድ ሃብት ክፍሎችን የመረጃ አሰባሰብና አያያዝ የሚያዘምን እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et
882 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:23:56
952 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:23:21 ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቅመ - ደካማ ቤቶች እድሳት ሥራ አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶች እድሳትሥራ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡
በማስጀመርያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ በከተማችን ውስጥ ከሚገኙ በርካታ አቅመ - ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጅሩ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የሦስት አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶችን ከ500 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የእድሳት ስራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
የቤቶቹ እድሳት ወጪም ከባለስልጣኑ ጋር አብረው የሚሰሩ የስራ ተቋራጮች እና ማህበራትን በማስተበበር የሚሸፈን መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፊኤል ብያብል በበኩላቸው ባለስልጣኑ እያደረገ ለሚገኘው ሰው ተኮር በጎ ተግባራት የምስጋናቸውን አቅርበው፣ ሌሎች ተቋማትና የህብረተሰብ ክፍሎችም በየአካባቢያቸው የሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችን ለማገዝ በበጎ ፈቃድ ተግባራት በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር መላ ሠራተኞቹን እና የስራ አጋሮቹን በማስተባበር የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤቶች የማደስ፣ ለችግር የተጋለጡ ህፃናትን የመደገፍ፣ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጥገና እና የደም ልገሣ ስራ ለማከናወን አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et
974 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 16:08:08
Addis Abeba city Roads Authority invites eligible bidders for the purchase of Asphalt grade 85/100
1.2K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 10:38:09
በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ በመንገድ ሃብት ላይ እየደረሰ ያለው ውድምት አሳሳቢ ሆኗል
ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ንጋት ላይ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ ይጓዝ የነበረ ባለተሳቢ ከባድ መኪና ባደረሰው አደጋ በአካባቢው በነበሩ 7 ተሽከርካሪዎች እና በመንገድ ዳር መብራት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
ከአሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት በተነሳ በሰው ህይወትና አካል ላይ እየደረሰ ካለው ጉዳት ባሻገር በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ የመንገድ መሰረተ-ልማቶች ላይ እያደረሰ የሚገኘው ውድመት አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በከፍተኛ ወጪ ተገንብቶ በቅርቡ በደማቅ ሥነስርዓት ተመርቆ በኦፊሴል ለትራፊክ ክፍት በተደረገው የአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ - ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ ተደጋጋሚ አደጋዎች እየደረሱ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ህግና ደንብ አክብራችሁ በመንቀሳቀስ እራስን ከአደጋና ከህሊና ፀፀት፣ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትና የመንገድ ሃብት ደግሞ ከውድመት በመታደግ የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንዲትወጡ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን መልዕክቱን ያስተላልፋል፡
1.3K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ