Get Mystery Box with random crypto!

ከአየር ጤና -ወለቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23 | AACRA

ከአየር ጤና -ወለቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአየር ጤና - ወለቴ ሱቅ- አለም ገና አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮንትራት ውል በዛሬው ዕለት ፈርሟል፡፡
ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 5.6 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይርጋዓለም ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት በ2 ዓመት ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ የኮንትራት ውል ፈርሟል፡፡ ጎንድዋና ኢንጂነሪንግ ደግሞ የማማከርና የቁጥጥሩን ተግባር የሚያከናውን ይሆናል፡፡
ነባሩ የአየር ጤና - ወለቴ መንገድ ተገቢውን የትራፊክ ፋሲሊቲዎችን ያላካተተ እና ወጥ የሆነ ስፋት የሌለው በመሆኑ አሁን ላይ እያደገ የመጣውን ከፍተኛ የትራፊክ መጠን ለማስተናገድ የማይችል ጠባብ መንገድ ነው፡፡
በዚህ ውል መሠረት የሚገነባው አዲሱ መንገድ ፈጣን የአውቶብስ መተላለፊያ መስመርን አካቶ የሚገነባ ከመሆኑም በተጨማሪ 4.5 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ እና ዘመናዊ የመንገድ ፋሲሊቲዎች እንዲኖረው ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et