Get Mystery Box with random crypto!

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቅመ - ደካማ ቤቶች እድሳት ሥራ አስጀመረ አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20 ቀን | AACRA

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቅመ - ደካማ ቤቶች እድሳት ሥራ አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶች እድሳትሥራ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡
በማስጀመርያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ በከተማችን ውስጥ ከሚገኙ በርካታ አቅመ - ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጅሩ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የሦስት አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶችን ከ500 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የእድሳት ስራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
የቤቶቹ እድሳት ወጪም ከባለስልጣኑ ጋር አብረው የሚሰሩ የስራ ተቋራጮች እና ማህበራትን በማስተበበር የሚሸፈን መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፊኤል ብያብል በበኩላቸው ባለስልጣኑ እያደረገ ለሚገኘው ሰው ተኮር በጎ ተግባራት የምስጋናቸውን አቅርበው፣ ሌሎች ተቋማትና የህብረተሰብ ክፍሎችም በየአካባቢያቸው የሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችን ለማገዝ በበጎ ፈቃድ ተግባራት በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር መላ ሠራተኞቹን እና የስራ አጋሮቹን በማስተባበር የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤቶች የማደስ፣ ለችግር የተጋለጡ ህፃናትን የመደገፍ፣ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጥገና እና የደም ልገሣ ስራ ለማከናወን አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et