Get Mystery Box with random crypto!

በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ በመንገድ ሃብት ላይ እየደረሰ ያለው ውድምት አሳሳቢ ሆኗል ዛሬ ረቡዕ ነሐ | AACRA

በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ በመንገድ ሃብት ላይ እየደረሰ ያለው ውድምት አሳሳቢ ሆኗል
ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ንጋት ላይ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ ይጓዝ የነበረ ባለተሳቢ ከባድ መኪና ባደረሰው አደጋ በአካባቢው በነበሩ 7 ተሽከርካሪዎች እና በመንገድ ዳር መብራት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
ከአሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት በተነሳ በሰው ህይወትና አካል ላይ እየደረሰ ካለው ጉዳት ባሻገር በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ የመንገድ መሰረተ-ልማቶች ላይ እያደረሰ የሚገኘው ውድመት አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በከፍተኛ ወጪ ተገንብቶ በቅርቡ በደማቅ ሥነስርዓት ተመርቆ በኦፊሴል ለትራፊክ ክፍት በተደረገው የአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ - ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ ተደጋጋሚ አደጋዎች እየደረሱ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ህግና ደንብ አክብራችሁ በመንቀሳቀስ እራስን ከአደጋና ከህሊና ፀፀት፣ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትና የመንገድ ሃብት ደግሞ ከውድመት በመታደግ የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንዲትወጡ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን መልዕክቱን ያስተላልፋል፡