[Forwarded from شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن] #ወጣቶች_ሆይ_አግቡ__!! ------------------------------------- #በዚህ_ዘመን_ያላገባ_ሰው #በሸይጣን_መረብ_ውስጥ_መከራን_ይጋታል!!! ☞ ሸይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን ሀፊዞሁሏህ ይላሉ፦ "ሴት ያለ ወንድ በመከራ ላይ ነች። ወንድም ያለ ሴት መከራ ውስጥ ነው። ተመጣጣኝ ጥንዶች በትዳር ከተቆራኙ የተሟላ ፀጋ ውስጥ ናቸው።" [اعانة المستفد (2/220)] ☞አል ኢማም አል ጁወይኒይ አሽ ሻፊዒይ ረሒመሁሏህ ይላሉ፦ "ላጤነት የእብደት ሰበብ እንደሆነ ሁሉ ኒካሕ እብደትን ከሚያስወግዱ ነገሮች አንዱ ነው።" [نهاية المطلب (12/43)] ☞ኢብኑ ዓባስ ረደየሏሁ አንሁ ይላሉ ፦ "አላህ ልጅ የሰጠው ሰው መልካም ስም ያውጣለት፤ በስነ ስርኣትም ኮትኩቶ ያሳድገው፤ ለአቅመ አዳም የደረሰ ግዜ ይዳረው!" [رواه ابن ابي الدنيا في العيال (443/1)] ☞ሱለይማን አር ሩሐይሊይ ሀፊዞሁሏህ ይላሉ፦ "ያለ ምንም ምክንያት ከማግባት የሚያፈገፍግ ሰው ወደ ሐኪም ጎራ እንዲል እንመክረዋለን" (منقول من محاضرة) ☞ሸይኽ ሙቅቢል አል ዋዲዒይ ረሒመሁሏህ ይላሉ፦ "እህትህን ወይም ሴት ልጅህን (ለጣሊበል ዒልም) የሸሪዓ እውቀት ተማሪ ለሆነ ወንድ መዳር ለአንተ ከዱንያና በውስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው!" [البشائر في السماع المباشر ص 13 ] ☞ሸይኽ አሕመድ አን ነጅሚይ ረሒመሁሏህ ይላሉ ፦ "ወንድ ልጅ መልካም ሴት ጋር ትዳር እስኪመሰርት ህይወቱ የተሟላና ደስተኛ አይሆንም። ሴትም እንደዛው።" [تأسيس الاحكام (4/172) ] ☞ታላቁ ታቢዒይ ጣውስ ረሒመሁሏህ ይላሉ፦ "እስኪያገባ ድረስ የአንድ ወጣት ዒባዳ አይሟላም" [السير (570/1)] ☞ታላቁ ታቢዒይ ኢብራሂም አን ነኸዒይ ረሒመሁሏህ ይላሉ፦ "አግባ! ቤቷ ሆና የሚመግባት ጌታ በአንተም ቤት አንተንም እሷንም ይመግባችኋል!" [تاريخ ابن محرز (150)] Copy From Nuredin al_arebi 49 viewsHabib Beshir አንደበትህንና ብዕርህን ለመልካም ነገር ተጠቀምበት!, 22:40