Get Mystery Box with random crypto!

ጎበዝ የኢትዮጲያ ብሄራዊ መዝሙር ተቀየረ መሰል¡ የዜግነት ቀብር ========== የዜግነት ቀብር | ሐቢቢ ሥነ_ፅሁፍ

ጎበዝ የኢትዮጲያ ብሄራዊ መዝሙር ተቀየረ መሰል¡

የዜግነት ቀብር
==========
የዜግነት ቀብር፣ በኢትዮጵያችን በዝቶ
ታየ ግፍ ጥላቻ ፣ ዳር እስከዳር ጎልቶ
ለበቀል ለበደል ፣ ለህዝቦች ባርነት
በአረመኔዎች እጅ ፣ ታርደናል በአንድነት
መሠረተ በቀል፣ ፍቅር እያዘመረን
ህዝቦች ነን በሴራ፣ ጅምላ የሚቀብረን
ድርቅ የርሀብ መድረክ፣ ጦርነት ማያጣት
የተፈጥሮ ገብያ፣ ሒያጅ መጪው ሚሸጣት
እንጠብቅሻለን፣ ሞተን በየተራ
ኢትዮጵያችን ኑሪ፣ እኛ ለአንቺ እንፍራ!

በላይ በቀለ ወያ