Get Mystery Box with random crypto!

*** ፀሐይ መውጣቷ አይቀርም! *** ጨለማው የቱንም ያህል ጥቅጥቅ ቢልም፤ ህይወት በጨለማ ውስጥ | የግጥም ረመጥ✍️

*** ፀሐይ መውጣቷ አይቀርም! ***

ጨለማው የቱንም ያህል ጥቅጥቅ ቢልም፤ ህይወት በጨለማ ውስጥ ምንም ያህል አስፈሪና አስጨናቂ ቢሆንም፤ ጊዜዋን ጠብቃ ፀሐይ ግን መውጣቷ አይቀርም።

ወዳጄ ሆይ አሁን ያለህበት ሁኔታ መውጣትና መውረድ ብቻ ከሆነብህ፤ ብዙ የሚያስጨንቁ ነገሮች በዙሪያህ ቢከቡህ፤ ህይወት አሰልቺ ብትሆንብህ አንተ ግን የዓላማ ሰው ሁን። ምክንያቱም ጊዜውን ጠብቆ የአንተ ልፋትና ድካም ለሌሎች ፀሐይ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ያን ጊዜ ሁሉም እንደዋዛ ያልፋል። ግን አንተ ከበረታህ ብቻ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!