Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ድል አደረገች ሀገራችን ኢትዮጵያ ግብፅን በፍፁም የበላይነት ድል አደረገቻት። የ | ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️

ኢትዮጵያ ድል አደረገች

ሀገራችን ኢትዮጵያ ግብፅን በፍፁም የበላይነት ድል አደረገቻት።

የዛሬውን ጨዋታ ለማስተናገድ ብቁ ሜዳ አጥታ በሰው ሀገር ማላዊ ከግብፅ አቻዋ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የተፋለመችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ግብፅን አሸንፋለች።

ሀገራችን ሙሉ ጨዋታውን በከፍተኛ የበላይነት ነው ያጠናቀቀችው።

ማላዊያን አንድም የግብፅ ሽንፈት ለሀገራቸው የሚሰጠውን ከምድብ የማለፍ እድልን ታሳቢ አድርገው በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሜዳ ውስጥ ባሳየችው ድንቅ እንቅስቃሴ ተስበው ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ ታይተዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገሩ እና ለኳስ ያለው ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል የዛሬው ጨዋታ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጎ ቢሆን አሁን ካለው የበለጠ ድባብ ይኖረው ነበር።

@tikvahethiopia