Get Mystery Box with random crypto!

መመሪያ ነው ድሮ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አንዲትን የገጠር ቀበሌ ሊጎበኙ ይወርዳሉ። በየደረጃ | ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️

መመሪያ ነው

ድሮ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አንዲትን የገጠር ቀበሌ ሊጎበኙ ይወርዳሉ። በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላትም አብረዋቸው ለዚህ ጉብኝት ይወርዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስተሩም ለጉብኝት የተመረጠችውን የአንዲት እናት ቤት ሲጎበኙ በኑሮዋ ዝቅተኝነትና በድህነቷ ክፉኛ ተነክተው ስቅስቅ ብለው ማልቀስ ይጀምራሉ። ይሄን የተመለከተው የክልሉ አስተዳደርም ማልቀስ ይጀምራል። የክልሉን አይቶ...የዞኑ...የዞኑን አይቶ የወረዳው መላቀስ ሆነ። ቀን በቀን አብሯት የሚኖረው ኑሮዋ ከአብዛኛው የቀበሌው ነዋሪ እንደማይለይ የሚያውቀውም የቀበሌው አስተዳደርም ግራ ገብቶት ወደ ወረዳው አስተዳዳሪ ጠጋ ብሎ የሚያለቅሱበትን ምክናያት ይጠይቀዋል። የወረዳውም አስተዳዳሪ አንገቱን እንደደፋና ፊቱን በእውሸት እንባ እንደረጠበ በሹክሹክታ እኝዲህ ብሎ መለሰለት

"ከላይ የወረደ መመሪያ ነው ዝም ብለህ አልቅስ"

@ZHabbesha @ZHabbesha