Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ zhabbesha — ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ zhabbesha — ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @zhabbesha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 307
የሰርጥ መግለጫ

አስተዋይ ሰው ማለት መቼ መናገር እንዴት መናገር ለምን መናገር የት ምን መናገር እንዳለበት የሚያውቅ ነው።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 08:59:43 "አንዳንድ ትዝታ አለ"

ዝምታችን ከዝምታ ገዝፎ በአረምሞ በተዘጋንበት ጊዜ ከዕዝነ ልቦናችን በኩል <<ኡኡኡ>>ብሎ የሚጮህ በዝግታ ካሳለፍነው የእድሜ ዘመን ቅፅበቶቻችን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ አልባችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነው ተናፋቂ ትዝታዎች መሃል ምናለ በደገምነው እያልን የምንመኘው ከትላንት ትዝታዎቻችን ጋር ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረው አንዳንድ ትዝታ አለ። እንደ ወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር። በእንባ በተሞሸርንበት ጊዜ እንኳን'በሀዘን ወህኒ ተወርውረን መረሳት፣ ክፉ አጋጣሚ ፊትለፊታችን ሲጋረጥ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ በእቅፉ የሚያስጠልለን አንዳንድ ትዝታ አለ። በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ

ያብስራ(ደብተራው)

@ZHabbesha @ZHabbesha
32 viewsIt's Me..., 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 19:19:12
172 viewsIt's Me..., 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 12:55:37 ሞትን መች ፈርተን እናውቃለን?

"እኛ መች ሞትን ፈርተን እናውቃለን? በሞታችን የሚሞቱ በሞታቸው የምንሞት ብዙ ሰዎች አሉ እንጂ እኛ መች ሞትን ፈርተን እናውቃለን ። ይልቅ ሞትን በፍቅር ተሳስበን እንግደለው። ቤት መቀመጥ ያቃተን መራባቸው የሚርበን ሰዎች ስላሉን እንጂ ቤት ጠፍቶን አደለም። ይልቅስ አብረን በር እንዝጋ እኛ እቤት ስንሆን ቀን ዳቦ ፍለጋ አደባባይ በሚሰፍሩት ዱኩማን ላይ ለሚዘንበው መከራ ማን ጥላ ይዘረጋል? ማንስ አቅም ኖሮት የሞት የሲቃ ዜናቸውን ለመስማት ከሳሎን ይቀመጣል? እባካችሁ አብረን በር እንዝጋ፣ አብረን እንሸመጥ፣ አብረን ቁርስ እንብላ አብረን ምሳ እንድገም። አለዚያ ይህም ታሪክ ሆኖ አስተዛዝቦን ያልፋል።ይህን ብለን እንጂ እኛ መች ሞትን ፈርተን እናውቃለን?"

@ZHabbesha @ZHabbesha
@ZHabbesha @ZHabbesha
290 viewsIt's Me..., 09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:12:12
ኢትዮጵያ ድል አደረገች

ሀገራችን ኢትዮጵያ ግብፅን በፍፁም የበላይነት ድል አደረገቻት።

የዛሬውን ጨዋታ ለማስተናገድ ብቁ ሜዳ አጥታ በሰው ሀገር ማላዊ ከግብፅ አቻዋ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የተፋለመችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ግብፅን አሸንፋለች።

ሀገራችን ሙሉ ጨዋታውን በከፍተኛ የበላይነት ነው ያጠናቀቀችው።

ማላዊያን አንድም የግብፅ ሽንፈት ለሀገራቸው የሚሰጠውን ከምድብ የማለፍ እድልን ታሳቢ አድርገው በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሜዳ ውስጥ ባሳየችው ድንቅ እንቅስቃሴ ተስበው ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ ታይተዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገሩ እና ለኳስ ያለው ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል የዛሬው ጨዋታ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጎ ቢሆን አሁን ካለው የበለጠ ድባብ ይኖረው ነበር።

@tikvahethiopia
202 viewsIt's Me..., 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 20:06:33 መመሪያ ነው

ድሮ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አንዲትን የገጠር ቀበሌ ሊጎበኙ ይወርዳሉ። በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላትም አብረዋቸው ለዚህ ጉብኝት ይወርዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስተሩም ለጉብኝት የተመረጠችውን የአንዲት እናት ቤት ሲጎበኙ በኑሮዋ ዝቅተኝነትና በድህነቷ ክፉኛ ተነክተው ስቅስቅ ብለው ማልቀስ ይጀምራሉ። ይሄን የተመለከተው የክልሉ አስተዳደርም ማልቀስ ይጀምራል። የክልሉን አይቶ...የዞኑ...የዞኑን አይቶ የወረዳው መላቀስ ሆነ። ቀን በቀን አብሯት የሚኖረው ኑሮዋ ከአብዛኛው የቀበሌው ነዋሪ እንደማይለይ የሚያውቀውም የቀበሌው አስተዳደርም ግራ ገብቶት ወደ ወረዳው አስተዳዳሪ ጠጋ ብሎ የሚያለቅሱበትን ምክናያት ይጠይቀዋል። የወረዳውም አስተዳዳሪ አንገቱን እንደደፋና ፊቱን በእውሸት እንባ እንደረጠበ በሹክሹክታ እኝዲህ ብሎ መለሰለት

"ከላይ የወረደ መመሪያ ነው ዝም ብለህ አልቅስ"

@ZHabbesha @ZHabbesha
213 viewsIt's Me..., edited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:53:26 "በመስመሩ መዘበራረቅ ውስጥ ህይወት አለ። መኖር ማለት ትክክለኛ እና ልክ አለመሆን ማለት ነው።ቀጥዩን እርምጃ ለመራመድ የምናነሳው እግራችን ሳይቀር በተዘበራረቁ መስመሮች ቀጥ ብሎ መራመድ ሲችል ህያው ሰው እንባላለን። ውጣ ውረድ በበዛብ አለም ውስጥ መረጋጋት ከድሎት እንጂ ከመኖር አያግድም። ህይወት በዝብርቅርቅ ምቾት መኖርን ታጎናፅፋለች። በመውጣትና በመውረድ በማግኘትና በማጣት በሰላምና በጦርነት መካከል የምንቀኘው የየግላችን የህይወት መስመር አለ"


@ZHabbesha @ZHabbesha
271 viewsIt's Me..., 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 05:16:26 "ሰላምን የምንኖርበት አንድ ሀገር ያስፈልገናል! ወደ ድሮ የቀረበ። በቴክኖሎጂ ያልደነቆረ። ሰው ከሰው የሚነጋገርበት። ተነፋፍቀን ፖስታ የምንፃፃፍበት። አንድ ትልቅ የሰላም ሀገር ያስፈልገናል። ገዳይ የሚገደልበት የሰለለ የሚቆረጥበት። ፍትህ ወደማይሽጥበት ወደዚያች ወደ ጥንቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ አንሰደድና የምንሳሳላቸውን ልጆች እንውለዳቸው"

@ZHabbesha @ZHabbesha
266 viewsIt's Me..., 02:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 06:22:29 "ገልፀህ ለማትጨርሰው ምግባርህ " እኔ ይሄ ነኝ" ብለህ እራስህን አታብራራ። መጥፎነትህን ለመሸፈን ካልሆነ በስተቀር ጥሩ ነኝ ተብሎ የራስ ተዓምር በራስ አይመሰከርም"


@ZHabbesha @ZHabbesha
256 viewsIt's Me..., 03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 15:32:02 "ሰው ራሱ ተስፋው በጭለማ ተከባ ተጀቡኖ እንደ ጢቢኛ እሳት መሃል ቢጣል የከበበውን እሳት ይረሳ ዘንድ ህይወት የተስፋ ውሃ የምታሳይበት አንዳች ሽንቁር አላት"

@ZHabbesha @ZHabbesha
240 viewsIt's Me..., 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 15:13:45
233 viewsMY NAME IS......., 12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ