Get Mystery Box with random crypto!

Adiss News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zenalerase — Adiss News A
የቴሌግራም ቻናል አርማ zenalerase — Adiss News
የሰርጥ አድራሻ: @zenalerase
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 642
የሰርጥ መግለጫ

#ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ማንኛውም መረጃ በሰዓቱ እናደርሶታለን ። የእርሶም አስተያየት እና ጥቆማ ለኛ ገንቢ ነውና በGroup https://t.me/Zenalers ያድርሱን። እናመሰግናለን 🙏

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 21:33:06 በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው አምባ ጊዎርጊስ ከተማ ከ 31ኛ ክፍለ ጦር እንደመጣ በመግለፅ ሶስት ኤርትራውያንን የጫነ ኮድ 06580 መ.ከ ሰሌዳ የመከላከያ ሰራዊት መኪና ለመፈተሽ ፈቃደኛ ባለመሆንና ኬላ በመጣስ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ወደ ጎንደር ከተማ እየገባ የነበረው ይህ መኪና የአካባቢው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያስቆሙት በሚሞክሩበት ጊዜ በቦታው የነበሩ እንስሳትን በመግጨት ሊያመልጥ ሙከራ አድርጓል።በማምለጥ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ከጎንደር ከተማ በ 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወለቃ ቀበሌ ላይ 3 ኤርትራዊያን የጫነው ሹፌር ከነመኪናው በመከላከያ ሰራዊት ኃይል ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ኤርትራውያንና የመኪናው አሽከርካሪ በጎንደር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

[Addis Zeybe]
@Zenalerase
46 views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:46:15 በደሴ ከተማ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለኤፍቢሲ እንደገለጹት ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የፖሊስ መረጃ እንደሚያመላክተው እስካሁን ድረስ ከ31 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ15 በላይ በቦታው ለሽያጭ የቀረቡ በጎች ሞተዋል።

@Zenalerase
81 views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:30:08 " ዕጣው ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት " ዳታው ገብቶ ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸው ይታያል በተባለው መሰረት የተወሰኑ ክፍተቶች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ምን ሊወስን እንደሚችል አልታወቀም ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ ጉዳዩና ውሳኔው ዛሬ ሊታወቅ ይችላል ሲሉም ጠቁመዋል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ 25,491 ሰው ዕጣ ወጥቶለታል ያሉት አቶ ሽመልስ ፤ ስህተት የፈጠረው ሰው እንደተለየው ሁሉ በስህተቱ እድሉ የተፈጠረለት ማነው የሚለው ተለይቶ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ የሚያሻግረው አማራጭ ይታያል ተብሎ እንደሚታመን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የተዝረከረከ አሰራር እንዳይኖር ቀድሞ ማጣራት ተደርጓል ያለው የቤቶች ኮርፖሬሽን ዳታው ከገባ እና ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸውን ገልጿል፤ ጉዳዩ እልባት ለማግኘት ተቃርቧል ሲልም አሳውቋል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።
@Zenalerase
87 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:47:57 "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው"

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ትሕነግ በአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈጸሙ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ይህንን ያሉት ከሰሜን ሸዋ ዞን የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በርካታ ጥቃቶች እየተፈፀመበት ነው ያሉ ሲሆን ጥቃቱን ማክሸፍ የሚቻለው በመደማመጥና በመተባበር ብቻ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ከውስጥም ከውጭም እየደረሱ ያሉ ጫናዎችን ለመቋቋም በሰከነ መንገድ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው" ብለዋል፡፡

ይህን መጠነ ሰፊ ጥቃትና ጥፋት የሚያቀናብሩትንና በክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም ባሉ አካባቢዎች እያደረሱት ያለውን የጥፋት አጀንዳ ለማክሸፍ ጠንካራ መንግሥታዊ መዋቅር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እየሠራን ነው ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ ለአብነት ከሰሞኑ በአጣዬና አካባቢው የደረሰው ጥቃት በተደጋጋሚ ረፍት ለመንሳት የሽብር ቡድኖች የጠነሰሱልን ሴራ አካል ነው ተብለዋል።

አሚኮ
@Zenalerase
100 views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:12:10 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደተቀሰቀሰ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በግጭቱ የሰው ሕይወት እንደጠፋና ንብረቶች እንደወደሙ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ግጭቱ የተፈጠረው ከአጣዬ ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ነው። ወደ ገጠር ቀበሌዎች ገብቶ ከመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የገባው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ የዓይን ምስክሮች ገልጸዋል።

Via:- Wazema
@Zenalerase
98 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:42:18 ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታዉቋል፡፡

አየር መንገዱ ለጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል ማሳየቱን ጠቁሟል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉና ከኢትዮጵያ የሚነሱ በረራዎች በአብዛኛው መጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

@Zenalerase
128 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:14:35
በምዕራብ ሸዋ ዞን በአሸባሪው ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ በርካቶች መደምሰሳቸው ተገለጸ

በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ሶስት ወራት በአሸባሪው ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ በርካቶች መደምሰሳቸውና እጅ መስጠታቸውን የዞኑ የአስተዳደርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በዞኑ አሸባሪውን ሸኔን ለመደምሰስ በተካሄደው ኦፕሬሽን የሽብር ቡድኑ በተለያዩ ጊዜያት የዘረፈው የሕዝብ ሀብት እየተመለሰ መሆኑንም አስታውቋል። በዞኑ ተጠናክሮ በቀጠለው ሕግ የማስከበር ኦፕሬሽን በተለያዩ ወረዳዎች 55 የአሸባሪው ሸኔ አባላት በሰላም እጃቸውን ሲሰጡ፤ 18ቱ መያዛቸውን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኦብሳ ሞቱማ ለኢዜአ ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው እንዳሉት በተለይ ባለፉት ሶስት ወራት በተካሄደው ኦፕሬሽን 109 የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 254 የሚሆኑት ላይ ደግሞ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። የዞኑ ሕዝብ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ኦፕሬሽን ተዘርፈው የነበሩ 251 የቀንድ ከብቶችና 120 በጎችና ፍየሎች ለባለንብረቶቹ መመለሳቸውን አስታውቀዋል። እንዲሁም 44 ሞተር ሳይክሎች፣ አንድ ተሽከርካሪ፣ 2ሺህ 100 ሊትር ናፍጣ፣ ከህብረተሰቡ የተዘረፈ ከ2 ሺሕ ኩንታል በላይ የምግብ እህል፣ ከ600 ሺሕ ብር በላይ መያዙን ተናግረዋል፡፡
#Share
@Zenalerase
151 views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:24:22 ኢድ ሙባረክ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል_አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳቹ ፣ አደረስን።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን!

መልካም በዓል *,
@Zenalerase
@Zenalerase
147 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:21:36 ቅዳሜ ሐምሌ 2/2014 ዓ.ም

መንግሥት ከደቡብ ክልል አምስት ዞኖች ያካተተ አዲስ ክልል ለመፍጠር ማቀዱን እንደሰማ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል። የአዲሱ ክልል መቀመጫ ሆሳዕና እንደሚሆን ዘገባው አመልክቷል። እንደ ዘገባው ከሆነ፣ አዲሱ ክልል የሚያቅፋቸው ዞኖች ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሃድያ፣ አላባ እና ከምባታ እንዲሁም የም ልዩ ወረዳ ናቸው። ጉራጌ፣ ስልጤ እና ሃድያ ከሁለት ዓመት በፊት የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ለማድረግ በምክር ቤቶቻቸው ማስወሰናቸው ይታወሳል።
#Share
@Zenalerase
168 viewsedited  05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:52:48
ሽንዞ አቤ ተገደሉ።

የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ተገደሉ።

ሺንዞ አቤ በምዕራባዊ ጃፓን በሚገኝና ናራ በተባለ ከተማ ጎዳና በአንድ ዕጩ ፖለቲከኛ ቅስቀሳ ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ ከበስተጀርባቸው በተተኮሰ ሁለት ጥይት ተመተው ነበር።

በኃላ ወደ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸዉን መታደግ አልተቻለም።

በቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ላይ ተኩስ ከፍቶ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገው የ41 ዓመት ግለሰብ ሲሆን በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉም ተዘግቧል።

Video Credit : Mia
@Zenalerase
200 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ