Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጲያ የኢንሹራንስ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ሊጨምር ነው በሚል ስለወጣው መረጃ አላውቅም ሲል የ | Zena Nebab ✅

በኢትዮጲያ የኢንሹራንስ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ሊጨምር ነው በሚል ስለወጣው መረጃ አላውቅም ሲል የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ሊጨምር ነው በሚል በአንድ መገናኛ ብዙሃን ላይ ስለወጣው ዘገባ ምንም አይነት መረጃ የለኝም ሲሉ ለአሃዱ ገልጸዋል፡፡

በባንኩ አሰራር መሰረት አዲስ ለሚመሰረቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የማቋቋሚያ ካፒታል አሁን በስራ ላይ ከሚገኘው የካፒታል መጠን ጭማሪ ቢደረግ እንኳን ከውሳኔ ሳይደረስ ጭማሪ ሊደረግ ነው ተብሎ ለህዝብ ይፋ አይደረግም ያሉት የባንኩ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን አሁን ላይ ዝርዝር ሁኔታውን ለማስረዳት የሚያስችል መረጃ የለኝም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ማቋቋሚያ ካፒታል 65 ሚሊየን ብር መሆኑ ይታወቃል፡፡

አሐዱ ራድዮ