Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፥ 'የዳቦ ዋጋን ተመን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር የለን | Zena Nebab ✅

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፥ "የዳቦ ዋጋን ተመን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር የለንም" አለ።

ቢሮ ይህን ያለው ለአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሚኤሳ በሰጡት ቃል ፥ በመዲናዋ በርካታ ነዋሪዎች የዳቦ ዋጋ በእጅጉ መጨመሩን እንዲሁም የዳቦው መጠንና ዋጋው እንደማይመጣጠን ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ ብለዋል።

በመዲናዋ ያሉ ከ 2 ሺህ በላይ ዳቦ ቤቶች ካለፈው 1 አመት ወዲህ ከንግድ ቢሮው ጋር የነበራቸውን ትስስር ያቋረጡ በመሆኑ አሁን ላይ ቢሮው የዋጋ ተመንን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

መንግስት የስንዴ ድጎማውን ማቋረጡን ተከትሎም በመዲናዋ ያሉ ከ 2ሺ በላይ ዳቦ ቤቶች ትስስራቸውን ማቋረጣቸውንም አስረድተዋል፡፡

አቶ ዳንኤል ፥ "ምንም እንኳን በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቅሬታ ቢያቀርቡም አሁን ባለው የቢሮው አሰራር ዳቦ ቤቶቹ ባስቀመጡት የዳቦ ግራም እና ዋጋ በትክክል እየሸጡ መሆን አለመሆኑን ቁጥጥር ይደረጋል እንጂ ዋጋ በመተመን በገበያው ጣልቃ መግባት አይቻልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አክለው በተያዘው አመት ባስቀመጡት የዳቦ ግራም መጠን ዋጋ ሲሸጡ ያልተገኙ ወደ 24 የሚጠጉ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
አሀዱ ኤፍ ሬድዮ