የተከበሩ አቶ አበባዉ ደሳለዉ ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ያቀረቡት ጥያቄ -የም/ቤት አባላትን ጨምሮ ማን | ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Picture 1 from ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal 2024-07-04 10:11:38
የተከበሩ አቶ አበባዉ ደሳለዉ ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ያቀረቡት ጥያቄ

-የም/ቤት አባላትን ጨምሮ ማንነትን መሰረት ያደረገ እስር ተፈጽሟል። አቶ ክርስቲያን ታደለ 1 አመት ለሚሞላ ጊዜ ታስረዋል። አቶ ታዬ ደንድዓ ፣ ዩሃንስ ቧያለዉ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር ለዉጡ ስህተት ፈጽሟል በማለታቸዉ በመሞገታቸዉ ብቻ ለወራት ታስረዉ ይገኛሉ። ሀብታሙ በላይነህ የተሰኘ የፌደሬሽን ም/ቤት እና የአማራ ክልል ም/ቤት አባል ሲሆን ላለፉት አራት ወራት የት እንደገባ አይታወቅም። ለመንግስት ሃላፊዎች አቤት ብንልም ምላሽ አላገኘንም። ምላሽ ይስጡን?

- በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢጠናቀቅም በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ ነዉ።የጅምላ እስር እየተፈጸመ ነዉ።

-መንግስት በህዝቡ ዘንድ እምነት አልገነባም ይህም የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ተከትሎ ነዉ። ባለፉት 10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ሀይሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የጅምላ ግድያን ፈጽመዋል። በመርዓዊ ፣ በደብረ ኤሊያስ ፣ ጅጋ ፣ ፍኖተሰላም ፣ ሰሜን ሸዋ ፣ ጎንደርና ወሎ የጅምላ ግድያዎች ተፈጽመዋል። ጾታዊ ጥቃት ፣ ድብደባ ፣ ዘረፋ እና ንብረት ማዉደምም ተፈጽሟል። እምነት ለመገንባት መንግስት ምን እቅድ አለዉ?

#ዳጉ_ጆርናል
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

@zena24now
41.53K ተመዝጋቢዎች
ዜና ምድብ
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገ...