Get Mystery Box with random crypto!

በገዳም ለሚገኙ ሴት መነኮሳት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ማሰባሰብ ተጀመረ የተፈጥሮ ፀጋ ለገዳማዉያ | ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

በገዳም ለሚገኙ ሴት መነኮሳት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ማሰባሰብ ተጀመረ

የተፈጥሮ ፀጋ ለገዳማዉያን ከራሴዉ ለራሴዉ በሚል መሪ ቃል በጎንደር ለሚገኘዉ በሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም እና በሌሎል ተመሳሳይ ከፍተኛ ችግር ባለባቸዉ ገዳማት ለሚገኙና በተፈጥሮ ምክንያት ንፅህና መጠበቂያ በማጣት ለተቸገሩ ሴት መነኮሳት የእርዳታ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ተጀምሯል።

ለዓለም ሞተዉ በክርስቶስ ፍቅር ህያዉ የሆኑት ገዳማዉያን መናንያን ከዓለማዊ ፈተና በላይ የተፈጥሮ ፀጋ እንቅፍት እየሆነባቸዉ መሆኑን በማንሳት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮችና መላዉ ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ እንዲያድርጉ ጥሪ መቅረቡ ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ተቋም አስተባባሪነት የተዘጋጀዉ ይህ መርሃ ግብር ከ40 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለገዳማዉያኑ ህክምና እንዲያደርጉ ለማድረግና በሚቀጥሉት 6 ወራት ለ 2000 ሴቶች 12ሺ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶችና 1ሺ ዳይፐሮች ለማቅረብ መታቀዱ በጋዜጣዊ መግለጫዉ ተጠቅሷል።

በዓይነት ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ከየካ ፓሊስ መምርያ ፊት ለፊት እልፍ ፀጋ ማዕከል በአካል በመገኘት ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል። በገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ በደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ተቋም ይፋዊ የንግድ እና የአቢሲንያ  የባንክ አካዉንቶች እንዲሁም በዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ በተዘጋጀዉ ጎ ፈንድ ሚ እጃቸዉን መዘርጋት እንደሚችሉ መገለፁን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በአብርሃም ፍቅሬ
#ዳጉ_ጆርናል