Get Mystery Box with random crypto!

ለ2016 በጀት ዓመት የተዘጋጀው የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ጸደቀ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤ | ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ለ2016 በጀት ዓመት የተዘጋጀው የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት የተዘጋጀውን 801 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

በጀቱ የጸደቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ሲሆን የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 ዓ.ም የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ዝግጅትን አስመልክቶ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርቧል።

የ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የተያዘ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 203 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብሩ ለካፒታል በጀት ተመድቧል፡፡

369 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፤ 214 ነጥብ 07 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ለክልል መንግስታት ድጋፍ እንደሚከፋፈል ተገልጿል።

ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ደግሞ 14 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን የፀደቀው በጀት ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ15 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለው ተብሏል።

#ዳጉ_ጀርናል