Get Mystery Box with random crypto!

“አዳሜና ሔዋኔ ሆይ…! '…ብር ቆጥቡ፣ በባንክ ማስቀመጥ ልመዱ የሚባለው እኮ ዝም ብሎ ለላንቲካ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

“አዳሜና ሔዋኔ ሆይ…!

"…ብር ቆጥቡ፣ በባንክ ማስቀመጥ ልመዱ የሚባለው እኮ ዝም ብሎ ለላንቲካ አይደለም። በደስታችሁ ጊዜ እንዲህ አውጥታችሁ እንደፈለጋችሁ ትበትኑት ዘንድ ነው። ብር እንዲህ የሚረገጠው፣ የሚዘራው በደንብ የባንክ ደንበኛ ሲኮን ነው። ባንክ ቤት ደንበኛ የሆነ ሰው እንዲህ በብር የመጫወት መብትም አቅምም አለው።

"…አሁንም አልረፈደም ሁላችሁም ፍጠኑ። ባንክ ቤትን እንደ ሸኔ ደጋግማችሁ ጎብኙ፣ ሥራ የለም፣ ገቢ ጠፍቷል፣ ብር ማግኘት አልተቻለንም ምናምን እያላችሁ ደግሞስ ምኑን እንቆጥብ እያላችሁ አታለቃቅሱ። አታላዝኑ። የጫካውን ሸኔ ተመልከቱ እንጂ። አያርሱ፣ አይዘሩ፣ አይቆፍሩ… እና ከየት አመጡ ልትሉ ነው…?

"…ደግሞ ይሄን እንደ አበባ፣ እንደ ፈንዲሻም የተበተነ የተዘራም ብር አይተህ በቄሮ ከባንክ ተዘርፎ፣ ሸኔም ሰው አግቶ የተገኘ የደም ገንዘብ ነው ብላብላ እያልላክ እኚኚኚኚ በልብኝ አሉህ። እኚኚብላ ሁላ… ቲሽ…

• በሉ እየተዘረፋችሁ…!