Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወሻ…! ፩ኛ፦ ቲክቶክ ደግሞ ምን እንደነካው አላውቅም Live እንዳልገባ መልሶ ከልክሎኛል። | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

ማስታወሻ…!

፩ኛ፦ ቲክቶክ ደግሞ ምን እንደነካው አላውቅም Live እንዳልገባ መልሶ ከልክሎኛል። ያው የፈረደበት ዲያቆን አማኑኤል ተጨቃጭቆ እስኪያስለቅቀኝ ድረስ ለዛሬ በቲክቶክ መንደር ሚሊዮኖች በጉጉት የሚጠብቁት መርሀ ግብር አይኖረንም ማለት ነው።

፪ኛ፦ መረጃ ቲቪን በተመለከተ የምሥራች አለኝ። በኤልያስ ክፍሌ በሥራ ምክንያት ክፍለሃገር ለክፍለ ሃገር መንከራተት የእለተ እሁድ "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የሚለውን ተወዳጅ፣ ደግሞም ተናፋቂ፣ ለወዳጅ ማርና ወተት፣ ለጠላት ሬትና በረኪና፣ የአይጥ መርዝም የሆነ መርሃ ግብሬ በቴክኒሽያን እጦት መቋረጡን፣ ቢያንስ 5 ወይም 6 ወራት ያህል ፕሮግራም ላይሮን እንደሚችል ነግሬአችሁ ነበረ።

"…ከፕሮግራሙ መቆምም ጋር ምንአልባት በሃገረ አሜሪካ ያላችሁ፣ በአይቲ ሙያ ዕውቀት ያላችሁ፣ የኤልያስን ቦታ ተክታችሁ የምታግዙኝ ካላችሁ አናግሩን ብዬም ነግሬአችሁ ነበር። በዚህ ጥሪ መሠረት እስከአሁን 5 ያህል ልጆች ፈቃደኝነታችሁን ያሳያችሁኝ መሆኑን ለኤልያስም ነግሬው እሱም ተደስቷል።

"…ስለዚህ በቁጥር በዛ ማለቱ አይከፋም በሃገረ አማሪካ የምትኖሩ እና ሌሎችም ፈቃደኛ የሆናችሁ ወንድም እህቶች ካላችሁ ፈቃደኝነታችሁን በውስጥ መስመር ንገሩኝ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በተገኘበት አንዲት አጭር ስብሰባ እናደርጋለን። የመብዛት ጥቅሙ አንዱ ባይችል አንዱ ይኖራል ማለት ነው። በዚያ ላይ ኤልያስ ክፍሌንም እናሳርፈዋለንም ማለት ነው።

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ከ1:00 ሰዓት ጀምሮ የሚመቻችሁ ወንድም እህቶች አናግሩኝ። ፍጠኑ።

• ፌስቡክ…
• ዩቲዩብ …
• ቲክቶክ…
• ራምብል…
• ቴሌግራም…

"…ቢሆንም እጅ መስጠት ብሎ ነገር አይታሰብም። ወደፊት ብቻ።