Get Mystery Box with random crypto!

ቀጠልኩ… '…አጠቃላይ ዘገባቸው ሲጨመቅ ትግሬ ሲበደል ዝም ብላችኋልና እሰይ ይበላችሁ… የ27 ዓ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

ቀጠልኩ…

"…አጠቃላይ ዘገባቸው ሲጨመቅ ትግሬ ሲበደል ዝም ብላችኋልና እሰይ ይበላችሁ… የ27 ዓመቱን ፋሽስታዊ ወንጀል በማረሳሳት ስለዐማራ የዘገቡ በማስመሰል በሆነች ዓረፍተ ነገር የዐማራ cause ላይ ውኃ በመቸለስ demoralized ለማድረግ መጣር።

፫ኛ፦ ለወያኔ የእንጀራ ቤት፣ የነዳጅ ጉድጓዷ የነበረውን አብዲኢሌን በመደገፍ በወያኔ ኮንትሮባንዲስት ጀነራሎች ጉሮሮ ላይ የተሰካ አጥንት የሆነውን አቶ ሙስጠፌንና በብአዴን ሰበብ ዐማራን በሆነው ባልሆነው መውቀጥ።

"…ለዚህ ነው በቀደም መጀመሪያ ሙስጠፌ ተመርዞ ዱባይ ሆስፒታል ገብቷል ብለው ያጮሁት። ዜናው በተሠራ ማግስት የኢድ በዓል ላይ ሙስጠፌ ጅጅጋ ላይ ታይቶ ውኃ ሲቸልሰባቸው ቆይተው ትናንት ደግሞ በዛው በሙስጠፌ ላይ አሁንም ሌላ የሙስና ክስ አመጡበት።

"…ሙስጦፌን አጀንዳ የሚያደርጉት እነሒዊ የአብዲሌ ክንፍ ስለሆኑ ነው። አብዲሌ ክልሉን የሂዊ ኮንትሮባንዲስቶች የሚፈነጩበት አድርጎት ነበር። ሚስጠፌ ደግሞ እንደ አብዲሌ አያሠራቸውም። አብዲሌ ጋዜጠኞቹን ስፖንሰር የሚያደርገው የህወሓት የገንዘብ ምንጭ ስለነበር ነው። ሂዊ የፌደራል መንግሥቱን ተጠቅማ ሙስጠፌን መምታት ትፈልጋለች። በዚህ ግርግር ሙስጠፌ ተወግዶ አብዲሌ ከተፈታላት ደግሞ እንደገና ተመልሳ ቀጠናውን ያዘች ማለት ነው። ኦህዴድ ደግሞ ዓይኑ እያየ ያንን ቀጠና ለሒዊ አሳልፎ መስጠት አይፈልግም። ሂዊ አውጥታው በኮንትሮባንድ ስትቸበችበው የነበረውን ነዳጅ አቢይ ሆዬ ገና ሥልጣን ላይ እንደወጣ ከነገ ጀምሮ ለገበያ እናቀርበዋለን ብሎ ሲበጠረቅ ኦሮሞዎቹ ተረባርበው እኛም ሳንዘርፍ የምን ጻድቅ መሆን ነው ዝጋ ብለው ዝም አሰኝተውት ይኸው ነገር ሁሉ ተዳፍኖ ቀርቷል።

"…አልጨረስኩም ተመልሼ እመጣለሁ። ምንደ ወያኔና ተጎታቹ ወነግ እንደ ጉድ ነው ያበዱብኝ። አይ ዘመዴ…