Get Mystery Box with random crypto!

'…ፊልም እና ሚዲያ ማለት እኮ ከአውቶሚክ ቦንብ የበለጠ አውዳሚም፣ አልሚም እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

"…ፊልም እና ሚዲያ ማለት እኮ ከአውቶሚክ ቦንብ የበለጠ አውዳሚም፣ አልሚም እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የአማሪካ ትልጉ የገፅታ ግንባታዋ ነፀብራቆች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል ሆልዊዶች የሚሠራቸው ፊልሞች እና እነ ሲኤንኤን የሚያመርቷቸው ወሬዎች መሆናቸው ይነገራል።

"…አንድ የሆልዊድ ፊልሞችን የሚያይ ሰው በዘመናዊ ካሜራዎች፣ በምርጥ ዳይሬክተሮች የተቀረፁ፣ የተፈበረኩ አምሳለ ገነት የመሳሰሉ ፊልሞችን ሲያይ ወዲያው ፊልሙን ማየት እንደጨረሰ ብድግ ብሎ እንጦጦ ኪዳነምህረት፣ ቅዱስ ዑራኤል በመሄድ የዲቪ ሎተሪ እንዲደርሰው ስለት የሚሳል ሰው የትየለሌ ነው። አሜሪካ ለማኝ ያለ፣ አውሮጳ ደሀ ያለ የማይመስለው ነፍ ነው። ሁሉም ሴቶች አንጀሊና ጆሊ የሚመስሉ የሚሰሉትም ነፍ ነው። ብር ከየዛፉ የሚሸመጠጥ የሚመስለውም የትየለሌ ነው። ይሄ የሆልዩድ ተጽዕኖ ነው።

"…የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሃንም እንደዚያው ነው የሚያደርጉት። የውሸት ዜና አምርተው ከመሸጥ እስከ መንግሥት መገልበጥ ድረስ አቅም ያላቸው ናቸው። ዋናው ሥራው የሚሠራው ጭንቅላት ላይ ነው። ከወደዱህ እንደወያኔ ደሴ ደርሰህ ኮተቤ ነህ ብለው ያጮሁልሃል፣ ካልወደዱህ ጨፍጫፊ፣ ምዕራብ ትግራይ እያሉ ሊያካልቡህ ታያቸዋለህ። ፈረንሳይ እየነደደች እንዲች ብለው አይዘግቧትም። የጠሉት ሃሀገር እና መንግሥት ከሆነና ለእነሱ ካልተመቻቸው ግን እንደ ሊቢያው መሀመድ ጋዳፊ አካልበው ወተትና ማር የሚያጠጣውን መንግሥቱን ገልብጦ እከካም እንዲሆን ያደርጉታል። ስለዚህ ሚዲያም አደገኛ ነው ማለት ነው።

"…ወያኔ ይሄን አሳምራ ታውቃለች። 27 ዓመት ቀጥቅጣ የገዛችው በሚዲያ ነው። ፓርቲዋን ገንብታ ተፈሪ የሆነችው በሚዲያ ነው። አቢይ ያን አይቶ ነው ጋዜጠኛና አክቲቪስት ላይ ኢንቨስት የሚያደርገው።

"…ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ…?