Get Mystery Box with random crypto!

'…በነገራችን ታች… '…በዚህ አካባቢ እየተካሄደ ያለውን የካርታ ጫወታ በደንብ እየተከታተልነው | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

"…በነገራችን ታች…

"…በዚህ አካባቢ እየተካሄደ ያለውን የካርታ ጫወታ በደንብ እየተከታተልነው ነው። ወፎቼም ውሎና አዳራቸውን በ4 ኪሎ መንበረ ፓትርያርክ ግቢ፣ በቦሌ ደንበል ህንጻ አጠገብ የኦሮሚያ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በለ ፔኒሲዮንና መቀሌ ከተማ እየንተንፈላሰሱ ሥራ ላይ ናቸው።

"…እኔና ወፎቼ በአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱሳዊ ጉባኤና ምስጢራዊ ሂደቱ ላይ በፍፁም ጣልቃ አንገባም። እነሱም ምርጫውን ምስጢራዊ እንዳደረጉት እኔም አስቀድሜ ምንም አልተነፍስም። ይግፉበት።

"…ቃል የምገባላችሁ ግን አንድም ከቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀኖና ውጪ በአቢይ አሕመድ፣ በሽመልስ አብዲሳ፣ በኦሮሚያ ወሐቢስት፣ በወለጋና በደቡብ ጴንጢስት በኪሳራዋ ወያኔም ፈቃድ የሚሾም ጳጳስ እንደማይኖር ነው።

"…አይ ሕዝቡ ምንአባቱ ያመጣል? ተብሎ የማንም ሸርሙጣ፣ አመንዝራ፣ ጋለሞታ፣ የማንም ወንድኛ አዳሪ፣ የማንም ወሴ፣ የተጠመቀ እስላም የአራት ሚስት ባል፣ የማንም ዘራፊ፣ ማፍያ፣ ጋጠወጥ ነውረኛ፣ የማንም ዘረኛ፣ ተረኛ፣ ወታደር፣ የማንም አቅለቢስ፣ ቀትረ ቀላል፣ ቀልበቢስ፣ ድልብ መሃይም፣ አራጅ፣ አሳራጅ፣ ነፍሰገዳይ አረመኔ ወንበዴ፣ የማንም ዘረኛ አስማተኛ ዶሮ ቀባሪ መተተኛ ግን አይሾምብንም። አበደን አይሾምብንም።

"…አይደለም እንዲህ ያለ ነውረኛ ሊሾምብን ቀርቶ አሁን ካሉት መካከል ያበጠውን እያፈነዳን ደፍርሶ እንዲጠራ እንፋለጣለን ላመጣላትም እንሞክራለን። የግድ ከሆነ ግን ጉዳዩ የሃይማኖት ነውና ይፍቱኝ አባቴ እያልን ወደ ፍልሚያው እንገባለን።

#ማስታወሻ፦ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሆይ አሜሪካ ድረስ ስሜን እየጠሩ ብዙ ባይደክሙ መልካም ነው። እኔ አሁን አልደረስኩብዎትም እርሶም ባይደርሱብኝ መልካም ነው። እርስዎ በተለየ የሚጠብቋት እኔ ዘመዴ የማፈርሳት ኢትዮጵያ የለችም።

•ይፍቱኝ አባቴ…!