Get Mystery Box with random crypto!

የዲቪ 2024 እድለኛ አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ! አሜሪካ ኢትዮጵያ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ከሰሞኑ አ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዲቪ 2024 እድለኛ አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

አሜሪካ ኢትዮጵያ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ከሰሞኑ አመልካቾች ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቧ ይታወሳል
የዲቪ 2024 እድለኛ አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ።
ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ ከሰሞኑ ማሳሰቡ ይታወሳል።
በዚህ መሰረትም አመልካቾች https://dvprogram.state.gov/ESC/ በዚህ ሊንክ በመግባት የዲቪ 2024 እድለኛ መሆን አለመሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለም የድቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ ኢምባሲው ማሳሰቡ ይታወሳል።
አመልካቾች ዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው በራሳቸው እና እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ብቻ ማረጋገጥ እንደሚችሉም ተገልጿል።
የ2023 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ ባሉት ቀናት ውስጥ እንደሚስተናገዱም ኢምባሲው በመግለጫው ላይ ጠቁሟል።
የ2022 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መከሰቱን ተከትሎ የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት በመሻከሩ ተጎድተናል ማለታቸው ይታወሳል።
ዲቪ ከደረሳቸው ኢትዮጵያዊያን መካከል አስተያየታቸውን ለአልዐይን የሰጡ የድቪ 2022 አሸናፊዎች በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻከር ምክንያት እድሉን ተጠቅመን ወደ አሜሪካ እንዳንሄድ ተደርገናል ብለውም ነበር።
በኢትዮጵያ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ በበኩሉ " የዲቪ ሎተሪ እድለኛ ተሆነ ማለት ቪዛ ይገኛል፣ ለቪዛ ቃለ መጠይቅም ይጠራል ወይም ቪዛ ይሰጣል ማለት አይደለም" ሲል በወቅቱ ምላሽ ሰጥቷል።
ነገር ግን የዲቪ ሎተሪ እድለኛ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ነው ያለው ኢምባሲው እድለኞቹ አሁን ላይ የቪዛ አገልግሎት ሂደት ውስጥ ሳይገቡ ከቀረ በቀጣይ በሚደረጉ ተመሳሳይ የቪዛ አገልግሎት ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ ሲልም አክሎ ነበር።
አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በድቪ ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
አፍሪካ የዚህ እድል ትልቁን ኮታ የምትሸፍን ሲሆን በዲቪ 2022 ፕሮግራም ግብጽ፣ አልጀሪያ እና ሱዳን እያንዳንዳቸው 6 ሺህ ሰዎች እድለኞች ሲሆኑ ሞሮኮ 4 ሺህ 138 ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ 3 ሺህ 347 ፣ጋና 3 ሺህ 145 ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 2 ሺህ 988 ሰዎች የዲቪ እድለኛ እንደሆኑ ከተቋሙ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። መረጃውን #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja