Get Mystery Box with random crypto!

ከ258 ሚሊዮን በላይ ዓለም ሕዝብ ለአስከፊ የምግብ እጥረት መጋለጡ ተሰማ ባለፈው የፈረንጆች ዓመ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከ258 ሚሊዮን በላይ ዓለም ሕዝብ ለአስከፊ የምግብ እጥረት መጋለጡ ተሰማ

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 2022 ከዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛ የሚሆነው በአስከፊ የምግብ እጥረት ውስጥ ማለፉን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአውሮፓ ሕብረት በጋራ የተቋቋመው የዓለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርትና የሰብዓዊ ድርጅቶች ጥምረት አስታወቀ፡፡

በዚህም 258 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ባለፈው ዓመት በአስከፊ የምግብ እጥረት መጋለጡን የገለጸው ተቋሙ፤ ይህ ቁጥር ከዓለም ሕዝብ ብዛት ሦስት በመቶ ይሸፍናል ብሏል፡፡

ለዚህም እንደ ምክንያት የተጠቀሰው የእርስ በርስ ግጭቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲሆን፤ በ58 አገራት የሚገኙ ከ258 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ነው የተባለው፡፡

በተለይ በሰባት አገራት ማለትም በሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ የመን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ናይጄሪያ፣ አፍጋኒስታን እና ሄይቲ የተከሰተው የምግብ ቀውስ ከኹሉም የከፋ በመሆኑ ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸው ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ በቀጠናው ከፍተኛ የምግብ ቀውስ እንዲፈጠር አድርጓል ተብሏል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሲንዲ ማኬይን በምግብ ዋስትና እጦት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጠቅሰው፤ አሁንም አፋጣኝ እርዳታ ካላገኙ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሯ ችግሩ በተለይም ድሃ በሆኑ አገራት በእጅጉ አስከፊ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ የከፋ የምግብ እጥረት ችግር ባለባቸው ሰባቱ አገራት አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja