Get Mystery Box with random crypto!

...ባል ና ሚስት በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

...ባል ና ሚስት በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ
ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰአታቸው ደረሰ፡፡
ድንገት ግን ባል አንድ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ለመታደም ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡
ሁሌ ደሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ የነገው ስብሰባ እንዳያመልጠው"
11 ሰአት ቀስቅሺኝ " ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው እና ወረቀት ላይ " ነገ የስራስብሰባ ስላለብኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለሁ፡፡
አደራ 11 ሰአት ላይ ቀስቂሺኝ" ብሎ በወረቀት ላይ ፅፎ እሷ የምታይበት ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡
ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3 ሰአት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋ ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ " 11 ሰአት ሞልቷል ተነስ ስብሰባው እንዳያመልጥህ " የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል፡፡
➧ማነው ስተት የሰራው? ማነውስ ልክ?
➧ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡ ዝምታ ደሞ መቼም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም፡፡
ወዳጆቼ ነገሮችን በንግግር ለመፍታት ሞክሩ።
መቻቻልን ይስጠን

#በቅንነት share ያድርጉት

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja