Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራ ሰራዊት ለሽረ ዕደስላሴ አዋሳኝ በሆኑት በሽራሮ እና ማይፀብሪ አካባቢዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የኤርትራ ሰራዊት ለሽረ ዕደስላሴ አዋሳኝ በሆኑት በሽራሮ እና ማይፀብሪ አካባቢዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ

ለሽረ ዕደስላሴ አዋሳኝ በሆኑት በሽራሮ እና ማይፀብሪ አካባቢዎች በኤርትራ ሰራዊት ተደጋጋሚ ትንኮሳ እየደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

ሰራዊቱ ከሽራሮ 17 ኪሎ ሜትር ድረስ ተቆጣጥሮ በመያዝ በርካታ ግፎችን በትግራይ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ የሽረ እዳስላሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ ተፈሪ ሀይለመለኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ የኤርትራ ሰራዊት ከፍተኛ ትንኮሳ በየቀኑ እንደደሚፈፅማባቸው አስታውቀዋል፡፡

የኤርትራ ሰራዊት በባድመ፣ ገምሀሎ እና በሽራሮ በኩል 17 ኪሎ ሜትር ድረስ በመዝለቅ ከብቶች የመዝረፍ፣ የመግደል እና ለእርሻ የተሰማሩ ሰዎች የመግድል እንቅስቃሴ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለም የተናገሩ ሲሆን፤ በማይፀበሪም በተለያዩ አከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ትንኮሳ እየደረሰበት እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ በዚህ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ የተማረረ መሆኑንም በመግለጽ፤ አሁንም ድረስ በሚድርስበት ጥቃት ክፉኛ እንደተጎዳ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥት በሰላም ስምምነቱ ላይ ባለው አመኔታ ነገሮችን በትዕግስት እያለፈ እንደሚገኝም ምክትል ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja