Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም የ994 የጥሪ ማዕከል አገልግሎቱን ለውስን ደንበኞች ብቻ ክፍት እንዲሆን አደረገ ኢ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኢትዮ ቴሌኮም የ994 የጥሪ ማዕከል አገልግሎቱን ለውስን ደንበኞች ብቻ ክፍት እንዲሆን አደረገ
ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ከጥሪ ማዕከል ሰራተኞች ጋር የሚገናኙበትን አገልግሎት፤ በከፊል የሚያስቀር አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ። በአዲሱ አሰራር መሰረት ከድርጅቱ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች ጋር የሚገናኙ ተገልጋዮች፤ “የፕሪሚየም እና የተለዩ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ” ተብለው የተለዩ ደንበኞች ብቻ እንደሚሆኑ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

መንግስታዊው የቴሌኮሚዩኒኬሽን አቅራቢ ድርጅት ከደንበኞቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ከሚሰጥባቸው አማራጮች ውስጥ አንዱ፤ ወደ ተቋሙ የጥሪ ማዕከል በ994 አጭር ቁጥር መወደል ነው። በዚህ ቁጥር ላይ የሚደውል ደንበኛ፤ በስልኩ ላይ በድምጽ የሚቀርብለትን አማራጮች በመከተል የሚፈልገውን የአገልግሎት አይነት እንዲያገኝ ይደረጋል። ደንበኞቹ ከተቋሙ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎችም፤ በመስመር ላይ የሚጠብቁ የጥሪ ማዕከሉ ሰራተኞች ምላሽ ይሰጣሉ።

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለጥሪ ማዕከሉ ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ “የፒን ቁጥርን ከመርሳት፣ የጥሪ ዝርዝርን ከመጠየቅ እንዲሁም ስልክ ቁጥር ከማስከፈት እና ከማዘጋት” ጋር የተያያዙ መሆናቸውን የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱላቸው የሚፈልጉ ደንበኞች መስመሩን ለረጅም ጊዜ ይዘው የሚቆዩ መሆናቸው እና ቁጥራቸውም በርካታ መሆኑ፤ ሌሎች “መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚጠይቁ ሰዎች” ከጥሪ ማዕከሉ ሰራተኞች ጋር እንዳይገናኙ ማድረጉን አስረድተዋል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja