Get Mystery Box with random crypto!

የቀጠለ 10) የሕወሓት ታጣቂዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ በጠለምት አምስት ንጹሃን ሰዎችን መግደላ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የቀጠለ
10) የሕወሓት ታጣቂዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ በጠለምት አምስት ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸው ተገለጸ፡፡  በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ ትናንት ሰኔ 08/2015 ድረስ ባሉት ቀናት አምስት ንጹኃን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ጠለምት ወረዳ ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ አለባቸው አለሙ፤ በጠለምትና ተከዜ ዙሪያ በሚንቀሳቀሱ በርካታ የሕወሓት ታጣቂዎች ንጽሃን መገደላቸውን እና ብዙዎችም መፈናቀላቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ስለሆነም የሕወሓት ታጣቂዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ እያደረሱት ያለውን ማንነት ተኮር በደል ለማውገዝ በጠለምት እና አካባቢው ዛሬ እሁድ ሰኔ 11/2015 ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

11) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ስምንት ዞኖች ሥር ባሉ 41 ወረዳዎች በተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ፤ 6 ሺሕ 159 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን እና ከእዚህም ውስጥ ከ70 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና ቁጥጥር እና ምርመር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገመቹ ሹሚ፤ በበሽታው ከሞቱት ከ70 በላይ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በሽታው የቆየባቸውና በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም ያልመጡ ብሎም ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል። 

12) በትግራይ ክልል ከሚገኙ 93 ወረዳዎች 26 ያህሉ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ውጭ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ መቀሌ ቅርንጭፍ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

የቅርንጫፉ ጊዜያዊ ኃላፊ ጸሐዬ እምባዬ፤ "ክልሉ ከኤርትራ እና አማራ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ያሉ 26 ወረዳዎች በኤርትራና አማራ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ናቸው።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። 

13) በአፋር ክልል አዋሽ አርባ ዞን አሚበራ ወረዳ የአፋር ክልል ፖሊስ አባል በመከላከያ ሠራዊት አባል መገደሉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ከመተሃራ ወደ አዋሽ አርባ፣ ወደ ድሬዳዋና፣ ሃረር የሚወስደው ዋና መንገድ መዘጋቱ ተገለጸ።

ለመንገዱ መዘጋት ምክንያት የሆነው አርብ ሰኔ 9/2015 ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የአፋር ክልል ፖሊስ አባል የነበረ አንድ ግለሰብ በመከላከያ ሠራዊት አባል በጥይት ተመቶ መሞቱን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባበት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለEMS Mereja ተናግረዋል፡፡
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja