Get Mystery Box with random crypto!

መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zebene_lemma — መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zebene_lemma — መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)
የሰርጥ አድራሻ: @zebene_lemma
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.68K
የሰርጥ መግለጫ

" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ሃይማኖት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን "
[ ሃይማኖተ አበው ]
For any comment @KENECOMBOT Contact us

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-07-13 07:50:49 ✥ የተቆለፈ ሳጥን

#ልዩ_ልዩ

አንድ በተቆለፈ ሳጥን ላይ ተቀምጦ የሚለምን ለማኝ ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀንም በዚያ መንገድ የሚያልፍ ሰው ወደሱ ጠጋ ብሎ ለመሆኑ የተቀመጥክበትን ሳጥን ከፍተህ ውስጡን አይተህ ታውቃለህን ? ብሎ ጠየቀው። ለማኙም አረ አላቅም አለና ከፍቶ ቢያየው ሳጥኑ በወርቅ በብር የተሞላ ነበር። እኛም እንደዛ ነን እኔ ዋጋ የለኝም አልረባም ብኖር ባልኖር። አልጠቅምም እንላለን። ግን አንድም ቀን ውስጣችንን አይተን አናውቅም። ውስጣችን ግን ወርቅ በመሰሉ አላማዎች እንቁ በመሰሉ በጎ ሀሳቦች የተሞላ ነው። ማይልስ እንዳለው የአለም ውድ ሀብት ያለው በአረብ ሀገራት የነዳጅ ቦታ ውስጥ አይደለም የአለም ውድ ሀብት ያለው በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ቦታዎች ውስጥም አይደለም ።የአለም ውድ ሀብት ያለው የመቃብር ቦታዎች ውስጥ ነው።

ምክኒያቱም ብዙዎች ወደዚህ አለም ይዘው የመጡትን አላማና ራዕይ አውጥተው ሳይኖሩትና ለአለም ሳያበረክቱት ስለሚሞቱ ነው። ማግኘት ማጣት የጊዜ ጉዳይ ነው። ማንም ባዶ የለም ምንአልባት አሁን ባዶ እጃችንን እንሆን ይሆናል ነገር ግን ባዶ ልባችንን አልተፈጠርንም። ለዝች አለም የምናበረክተው አንዳች ነገር በውስጣችን አለ። እኛ ምን አልባት ለቤተሰቦቻችን በስህተት የተወለድን ይመስላቸው ይሆናል። ነገር ግን በስላሴ ዘንድ መለኮታዊ አጀንዳ ተይዞልን ለአለማ ተወልደናል። አለም ላይ ላሉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ የያዝን አለን: ለተዘበራረቀው ፖለቲካችን የተስተካከለ የአመራር ብቃት ያለን አለን ፡ እየጠፉ ላለው ስነፅሁፋችን የተባ ትንቱግ ብዕር የጨበጥን አለን ፡ ብቻ ሁላችንም ውስጥ ውድ ሀብት አለ። እኛ ግን ቆልፈንበት ተቀምጠናል እናውጣው እንጠቀምበት

#መልካም_ቀን
________

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ    
5.6K viewsedited  04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:40:10
ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
5.6K viewsedited  11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:21:25
እንኳን አደረሳችሁ!

እነሆ ሐምሌ 5 በዚህች ዕለት የዓለም ብርሃናት የሆኑት ጴጥሮስና ጳውሎስ ቅድስት ስለሆነች ሃይማኖታቸው ሰማዕትነትን ተቀበሉ። ጳውሎስ አንገቱን ሲቆረጥ ጴጥሮስ ቁልቁል ተሰቀለ።
በረከታቸው ይድረሰን!

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
7.4K viewsedited  05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:30:11 ​​​​ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል።

የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19)

ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።

ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ።

ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።

ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው።

ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
7.2K viewsedited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:43:45 ​​ወበዛቲ ዕለት ሐምሌ ፭ “ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ”

ክበር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር፤ (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ. ፻፲፭/ ፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15)

“ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።” ማቴ.፲፫፡፲፩

እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታቱ ለቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት ቀን በዓላቸው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ አሜን።

ቅዱስ ጴጥሮስ

ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኰኩሐ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ ስምዖን ነው። ዮሐ.፩፡፵፭ (1፥45)፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል። እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መነኸርያ በነበረችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡

ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ይተዳደር የነበረው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ነበር። ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗለ። ማቴ. ፬፡፲፱ (4:19) ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን ዕዳ በዕዳ ከተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋያ ነውና ሮምን ደርቦ ሰርቶታል።

በሮምም ፳፭ (25) አስተምሯል። ከዚያ በፊ ግን በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣በቀጳዶያና በቢታኒያ አስተምራል። በትምህርቱም ጣቢታ ከሞት አስነስቷል። ሐዋ. ፱፡፴፪-፴፬ (9፡32¬-34) ያስተማራቸው ምዕመናም ከሃማኖታቸው እንዳይወጡ ፪ (2) መዕክታትን ጽፎላቸዋል። ንጉሱ ኔሮን ቄሳር ጣኦት አምላኪ ነበርና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር። ለጣዖትም እንዲሰግድ ባስገደደው ጊዜ ለጣኦ አልሰግድም በማለቱ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት።

አይሁድ ሲጣሉት ወደ ጌታ ቢያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር። ይዞ ዳግም ቢሰቅሉትም ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው። በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅሎታል። ሥጋውን ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንቦ እንዳይፈርስ በማረ በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል።

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
7.7K viewsedited  11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:38:01 "#ደኅና_ነው" መጽሐፈ ነገስት ካልዕ 4:23

ሱነም ተብላ በምትጠራ መንደር ትኖር የነበረች "ሱነማዊት" ለእግዚአብሔር ሰው ነብዩ ኤልሳዕ መልካም በማድረግ ከባሏ ጋር ትተባበር ነበር። ይህች ደግ ሴት ልጅ አልነበራትም። ነገር ግን ከወገኖቿ መሐል ስለምትኖር ታመሰግናለች እንጂ አታማርርም።

እግዚአብሔር በነብዩ ኤልሳዕ አማካኝነት የመካንነት ጥማቷን በልጅ አረካና ጎዶሎዋን ሞላላት። ልጇን በደስታ እያሳደገች ባለበት ሁኔታ ከቀናት በአንዱ ቀን በራስ ህመም ታሞ በክንዷ ላይ ሞተ። መሞቱን ከእርሷ ውጪ ያየ ስላልነበረ በፃዲቁ ሰው አልጋ ላይ አስተኝታው በር ቆልፋበት የእግዚአብሔርን ሰው ልትዋቀሰው እግሮቿን አፀናች።

ይህች ሴት ነብዩ ኤልሳዕን እስክታገኘው ድረስ በመንገድ ስለ ልጇ ደኅንነት ለሚጠይቋት ሁሉ "ደኅና ነው" እያለች ትሄድ ነበር። ነብዩ ኤልሳዕን ስታገኘው ግን የሆነውን ብትነግረው የሚሆነውን አደረገላት። የሞተው ልጇ ተነስቶ እንደቃሏ "ደኅና" ሆነላት።

"ለሁሉም ካብራራህ ችግርህን ታገዝፈዋለህ"

ከልጅ ሞት በላይ የጠነከረ ደንዳና ሀዘን ምን አለ? እንዲህ በገዘፈ ሀዘን ውስጥ ሆኖ የሞተን ሰው "ደኅና ነው" ማለት ጠላትን ማስደገጥ ያክል ነው። ጠላት ማሸነፉን ከሚያረጋግጥባቸው ነገሮች አንዱ ደኅና አይደለሁም የሚል ቃል ከአፋችን ማዳመጡ ነው። ቅዱሳንን ሁሉ "እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ "መጽሐፈ ኢዮብ 24:23

ነገሮች ባይሳኩልኝም እኔ ደኅና ነኝ። አለኝ ያልኩት ባይኖረኝም እኔ ደኅና ነኝ። ወዳጅ እንደ ተልባ ስፍር ተንሸራቶ ቢወርድም እኔ ደኅና ነኝ። ሃብት ንብረቴ
በሰው የሚቆጠር ባይሆንም እኔ ደኅና ነኝ። አግኝቼ ባልስቅም እኔ ደኅና ነኝ።
ከሳሾቼ እንደ ፈረስ ኮቴ እርምጃቸው ቢያስፈራም ደኅና ነኝ። በጋጥ ውስጥ ከብቶች ባይኖሩኝም እኔ ደኅና ነኝ።

"አስተውሉኝ የእኔ ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ደኅና ነኝ ማለትን በሕይወት እንደ ሱነማዊቷ ስንለምድ የጠላትን ምሽግ የማፍረስ አቅም ይኖረናል"

እግዚአብሔር ሁሉን ደኅና ያድርግልን።
_________________________________

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
7.3K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:35:14
9.0K views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:35:14
8.5K views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:35:14
7.5K views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:34:45
እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ የመርሐግብራችንን ትኬት ለ3 ቀናት መሸጥ እንጀምራለን። ከዛሬ አርብ ከሠዓት ጀምሮ ማለት ነው እናም ያሉን ትኬቶች ጥቂት በመኾናቸው በየ አቅራቢያችኹ ትኬቶቹን እንድትገዙ ይኹን! ትኬቶቹን
1. በሁሉም አብያተ ክርስቲያን
2. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋየ ቅድሳት መሸጫ
3. በአቤላክ የመጻሕፍት መደብር
4. በዲቫይን ስፓርክ የኮምፒዩተርና ቋንቋ ት/ቤት
5. በባኮስ ሱፐር ማርኬት እንዲሁም ለበለጠ መረጃ በ09 02 88 67 83 ላይ በመደወል ትኬቱን በእጆ ማስገባት ይችላሉ።

ኑ በእውቀት፣ በምግባር እና በሃይማኖት የጸና ሰው በጥበብ እንገንባ!
7.8K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ