Get Mystery Box with random crypto!

መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zebene_lemma — መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zebene_lemma — መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)
የሰርጥ አድራሻ: @zebene_lemma
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.68K
የሰርጥ መግለጫ

" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ሃይማኖት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን "
[ ሃይማኖተ አበው ]
For any comment @KENECOMBOT Contact us

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-06 13:42:51
የነነዌ ጾም ሥርዓተ ጸሎት መርሐ ግብር

ምዕመናን ለጸሎት ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ከጸሎት መጽሐፍት ውጪ ሌላ ምንም አይነት መፈክር ይዘው እንዳይመጡ ቅዱስ ሲኖዶስ አሳስቧል።

ምንጭ: EOTC TV
4.7K views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 15:51:04 ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጂማ ከተማ በፀጥታ አካላት ተወሰዱ
**

ብጹዕ አቡ
ነ እስጢፋኖስ የጅማ፣ የየም፣ የኮንታ፣ የዳውሮ፣ የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መላከ ሰላም ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል አሰፋ እና የሀገረስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ማምሪያ ኀላፊ ላዕከ ወንጌል ባዬ ከድር ከጅማ አየር ማረፊያ  ዛሬ 7 ሰዓት ላይ ፖትሮል በያዙ አካላት ወደ ጅማ ፖሊስ መምሪያ የተወሰዱ ሲሆን እስካሁንም አልተለቀቁም።
9.8K views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 12:21:59
" በዚህ ሕገ ወጥ ሂደት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የተከበሩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጥቃትና፣ የባህልና የሃይማኖት ቅርሶችን ስርቆትና ዘረፋን ለመከላከል ኃላፊነት ያለበት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት ነው"
የሰሜን አሜሪካን የሲቪክ ማኀበራት ምክር ቤት

የሰሜን አሜሪካን የሲቪክ ማኅበራት ምክር ቤት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለሁለት ለመክፈል ታስቦ በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ሳይጠብቅ የተከናወነውን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመቃወም መግለጫ አውጥቷል።

የሰሜን አሜሪካን የሲቪክ ማኅበራት ምክር ቤት የተሞከረውን መፈንቅለ ሲኖዶስ በጽኑ በማውገዝ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ በአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከሚመራው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር አጋርነታችንን እናረጋግጣለን ብሏል መግለጫው።

በተጨማሪም የሲቪክ ማኅበራት ምክር ቤቱ በዚህ ሕገ ወጥ ሂደት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የተከበሩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጥቃትና፣ የባህልና የሃይማኖት ቅርሶችን ስርቆትና ዘረፋን ለመከላከል ኃላፊነት ያለበት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራው መንግሥት መሆኑን አስታውሶ። ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ በማቅረብ በዚህ ፈታኝ ጊዜ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚቆም በመግለጫው ጠቅሷል። መረጃው የኢኦተቤ ቴቪ ነው፡፡
11.7K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 14:55:45 የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባ ቶማስ የቂሊያ ሜትፖሊታን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ።

ምንጭ: EOTC TV
12.3K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 14:55:45
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማይቀበል የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአቋም መግለጫው አስታውቋል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ
ልዩ ጽሕፈት ቤት፣

ካይሮ፡ 24 ጃንዋሪ 2023 ዓ/ም (ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም)
የአቋም መግለጫ

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አቡነ ሳዊሮስ በተባሉ ጳጳስ የተፈጠረውን ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ራሳቸውን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ፓትርያርክ አድርገው የመሠየም ተግባር ሙሉ ለሙሉ የማይቀበለው ፍጹም ሕግን የጣሰ መሆኑና እና በእሳቸው መሪነት ተሾሙ የተባሉ 26 ጳጳሳት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሱ እንዲሁም መሠረት ያለውን እና ቋሚ የሆነን ከጥንት ጀምሮ በትውልዱ ሁሉ ሲተላለፍ ከመጣውን ከኦርቶደክስ ቀኖና እና መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ዕውቅና ውጭ የሚደረግን ሢመት ዕውቅና አትሰጥም አትቀበልም።

ከዚህ በተጨማሪ ኮሚቴው (የውጭ ጉዳይ) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት እየገለጽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፤ ሜትሮፖሊታን የሆናቸሁ ሁላችሁ ጥንታዊነት እና በታሪክ የበለጸገች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ትሥሥር በፍቅርና በሰላም ሁናችሁ እንድትጠብቁ በጥብቅ አደራ እንላለን፡፡
12.8K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 20:08:39 ​​#ህዳር 6

+በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው።

ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹ ወደ #ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው ""ያቺ የተባረከች ሀገር ናት"" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!!ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰቷታል በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ታምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት አለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ! የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን !! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !!
ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡

ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡

ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!

«ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ...ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

@ortodoxmezmur
5.0K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 20:08:39
ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡
4.4K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 09:46:36 +• የቀስት ጸሎቶች •+

የጊዜ ባለቤት ለሆነው ፈጣሪያችን "ጊዜ አጣሁ" ማለት ከጀመርን ሰንበትበት ብለናል:: የፈጣሪን በረከት መንዝረን ስናበቃ ለእርሱ የሚሆኑ ሽርፍራፊ ደቂቃዎችን ለመመደብ እናመነታለን:: አባቶቻችን እና እናቶቻችን "ጸልዩ! ኧረ ተዉ ጸልዩ!" ብለው ለዘመናት ወተወቱ:: ይህ ምክራቸው ግን ፍጹም ሰሚ አጣ:: በጊዜ ያልተካንነውን ጸሎት ሁሉም ጭንቅ ሲሆን በወከባው መሃል ለመጸለይ ብንፈልግም ተሳነን:: "ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ" እንደሚባለው ሠርግ የተባለ ሞት ደርሶ ስንኳ በርበሬ መቀንጥሱን አልቻልንም:: በተጋድሎው እጅግ ደክመን በመንፈሳዊው ውጊያው ላይ ሰይጣን ሙትና ቁስለኛ እያደረግን አለን::

ከትእዛዛቱ ምን ያህል እንደራቅን የምናውቀው "ሳታቋርጡ ጸልዩ" (1 ተሰ 5:17) መባላችንን ስናስታውስ ነው:: ጸሎቱ እንዳይቋረጥ የታዘዘው ውጊያውም ስለማያቋርጥ ነው:: ሰይጣን ድካም የሌለበት፣ እንቅልፍ የማያስፈልገው፣ ተስፋ የማይቆርጥ እና የብዙ ሺህ ዓመታት የሥራ ልምድ ያለው ከይሲ ነው:: የእኛን የሰዎችን ሁኔታ በሚገባ ስለተገነዘበም ቀጥታ ከመግጠም ይልቅ እንደ ደፈጣ ተዋጊ እየተደበቀ፣ እያዘናጋ እና እያደባ ያጠቃናል:: "የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።" (ኤፌ 6:11) የሚለው ቃል አንድም ሳይቀር ያሉንን መንፈሳዊ ትጥቆች ሁሉ ታጥቀን እንድንነሳ የሚያሳስብ ነው:: ይህ የውጊያውን ብርቱነት በአጽንኦት ያስታውሰናል::

የጥንቶቹ ብርቱ አባቶች እና እናቶች ሰይጣንን እያቆሰሉ ድል ከነሱበት መሣሪያ አንዱ የቀስት ጸሎት ነው:: የቀስት ጸሎት ማለት ከመንፈሳዊ መጻሕፍትም ሆነ ከራሳችን ሊገኙ የሚችሉ አጭር እና በተመስጦ የሚባሉ አጫጭር ጸሎቶች መጠሪያ ነው:: በተለይም ደግሞ የምንኩስና ተጋድሎ በተፋፋመበት የግብጽ በረሃ ከጥንት አንስቶ የዚህ አይነት ጸሎቶች ጥቅም ላይ ይውሉ እንደነበር የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ:: አባ ፖላሞን ከርሱ በቀደሙ ብርቱዎች ትምህርት ላይ ተመስርቶ አባ ጳጉሚስን ሲያስተምረው "ሳናቋርጥ እንድንጸልይ ታዝዘናልና፤ አጫጭር ጸሎቶቹን ሳንቆጥር ልንጸልይ ይገባናል" ብሎት ነበር:: ታላቁ ቅዱስ ወግሪስም "አጭር የተመስጦ ጸሎቶችን ተጠቀሙ" በማለት የሚመክር ሲሆን የእነዚህ ጸሎቶች ኃያልነትም ይታይ ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘአስቄጥስ አጭርና በተመስጦ የሚባሉት ጸሎቶቹ ሰይጣንን ሲያቆስሉት በራዕይ ተመልክቶ ነበር::

ከእነዚህ የቀስት ጸሎቶች መካከል "ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ" የሚለው ጸሎት ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው:: ይህ ጸሎት በተለያየ አይነት ሁኔታ ለዘመናት አገልግሎት ላይ ውሏል:: በሀገራችንም "እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ" (አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን) በሚለው ይታወቃል:: እንዲህ አይነት ጸሎቶች በሀገራችን የምንኩስና ታሪክ ውስጥ እንደነበሩ ማሳያ ከሚሆኑት አንዱ ደግሞ ቅዱስ አቡነ ሃብተማርያም ናቸው:: የታላቁ አቡነ ሃብተማርያም ገድል እንደሚነግረን ከሆን አባታችን ይህንን ጸሎት ከሰሙበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር እየደጋገሙ ይጸልዩት ነበር:: ዛሬም ድረስ ከመነኮሳት እስከ ምእመናን ድረስ ተወዳጅ ጸሎት ሆኖ እንደቀጠለ ነው::

የቀስት ጸሎቶች ሰይጣንን እረፍት ይነሱታል:: የእኛን ኅሊና ደግሞ ሁሌም ከፈጣሪ በማገናኘት "አልእሉ አልባቢክሙ" (ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ) የሚለውን ሰማያዊ ትእዛዝ ፈጻሚ ያደርጉናል:: የጸሎት መጽሐፍ መጨበጥ በማንችልባቸው ጊዜያት ሁሉ ከፈጣሪ የምንገናኝባቸው ድልድዮች ናቸው:: ከእነዚህ አጫጭር ጸሎቶች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት:-

* ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ

* አቤቱ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ፤ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ (መዝ 50:10)

* አቤቱ ጌታዬና ንጉሤ ሆይ፤ ለባልንጀሮቼ ክፉ ያለማሰብን እና የራሴን ኃጢአቶች የማየት ጸጋ ስጠኝ (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

* አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ተመልከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን። (መዝ 70:1)

* ጌታ ሆይ፤ እንደ ፈቃድህ እና እንደ እውቀትህ ማረኝ! (ቅዱስ መቃርዮስ)

* ጌታ ሆይ እርዳኝ!

የሚከተሉት ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከደረሳቸው የሃያ አራት ሰዓት አጫጭር ጸሎቶች መካከል የተመረጡ ናቸው:-

* አቤቱ ጌታ ሆይ፤ ከዘለዓለማዊ ስቃይ አድነኝ!

* እቤቱ ጌታ ሆይ፤ ከፈተና ሁሉ አድነኝ!

* አቤቱ ጌታ ሆይ፤ አትተወኝ!

* አቤቱ ጌታ ሆይ፤ ትሕትናን፣ ንጽሕናን እና መታዘዝን ስጠኝ::

* አቤቱ ጌታ ሆይ፤ ስምህን አመሰግን ዘንድ ጸጋህን ላክልኝ::

* አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ በሕይወት መጽሐፍ ስሜን ጻፈው፤ መጨረሻዬንም አሳምርልኝ::

በእነዚህ እና መሠል ጸሎቶች ሕይወታችንን እናስጊጥ:: ለመጸለይ የግድ ሰዓት መጠበቅም ሆነ የጸሎት መጽሐፍ መጨበጥ የለብንም:: ልባችን ያረፈበትን አንድ አጭር ጸሎት (ወይም እንዳለንበት ሁኔታ ተስማሚ የሆነውን አጭር ጸሎት) የእግር ጉዞ ስናደርግ፣ በመኪና ስንሄድ፣ ስንቀመጥም ሆነ ስንተኛ በውስጣችን እየደጋገምን እንጸልይ::

ጸሎት የሁሉ ነገር መክፈቻ ቁልፍ መሆኗን አንዘንጋ!

Fresenbet G.Y Adhanom
3.2K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:29:33 ኦ ሚካኤል!

ሚካኤል ሆይ፤ የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም አጠራርህ ጋር ለተባበረ ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡ የእግዚብሔር የምክሩ አበጋዝ ሆይ፤ የተቸገሩትን፣ የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ፤ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ በፍጥነት ድረስልኝ፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ሚካኤል ሆይ፤ በጠላት ተማርከው ለሚጨነቁና ለሚሰቃዩት ዋስ ጠበቃቸው አንተ ነህና፡፡ በእኔ ላይ የሚተበትቡትን የጠላቶቼን የምክር መረብ በጣጥሰህ ጣልልኝ፡፡ ነፍሴንም ሥጋዬንም ለአንተ አደራ ሰጥቻለሁና፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በተደረገ ጊዜ የዘለፋ ቃል ላልተናገረ አንደበትህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡር መልአክ ሆይ፤ ክብርህ ከመላእክት ሁሉ ክብር ከፍ ያለ ነውና፤ በሥነ ሥዕልህ ፊት ቆሜ ልመናዬን በማቀርብበት ጊዜ ሁሉ አይዞህ አለሁልህ በማለት ፈጥነህ ድምጽህን አሰማኝ፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ የፍጥረታት ሁሉ መጠለያ ለሆኑ ክንፎችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡር የሰማውያን ካህናት አለቃ ሆይ፤ ከእለት እኪት አድነን፤ ከጥፋት ሁሉ ሰውረን፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ የመብረቅ መስቀል ምልክት ያለበት በትረ ወርቅ ለጨበጡ እጆችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ሊቀ መላእክት ሆይ፤ በገዳመ ራማ የምትኖር የዋህ ርግብ ወይም ዋልያ አንተ ነህና፤ የሕጻናት እድገት በነጋው በነጋው እንዲጨምር ጽድቅህ በእኔ በባርያህ ላይ እድገቷን ታሳይ፤ ትግለጽ፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ ቂም በቀል የሌለበት የርህራሄ እና የየዋህነት መዝገብ ለሆነ ልቡናህ ሰላም እላለሁ፡፡ የሰማያዊያን ኃያላት አለቃ ሚካኤል ሆይ፤ የእስራኤልን ልጆች ባሕሩን ከፍለህ በባሕር መካከል እንዳሳለፍካቸው፤ እኔንም አገልጋይህን ከስውር ወጥመድ ሰውረህ በሰላም አሳልፈኝ፡፡

አማላጃችን ሚካኤል ሆይ፣ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ፣ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህኮ፡፡ የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህኮ፡፡ ይልቁንም የልዑላን ልዑል አንተ ነህና፤ በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታህ በቸርነትህ ድረስልኝ፣ አትራቀኝ፡፡
7.6K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 09:26:42
.
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ እረፍት በሠላም አደረሰን!


#ሼር
__

#share #share

https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ    
11.1K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ