Get Mystery Box with random crypto!

የምሥጢሩ ቁልፍ        በ1900 ከክርስቶስ ልደት በፊት አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመ | Yoni Arts

የምሥጢሩ ቁልፍ
    
  በ1900 ከክርስቶስ ልደት በፊት አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሐይን ለመዞር ስንት ጊዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን
ጽፏል።

NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።

አሐሜኔስ መዝገበ ሰማያትና አውደ ከዋክብት የተባለው መጽሐፍ በታወቀው ቦታ ዋልድባ የሚገኝ ሲሆን ይኸው መጽሐፍ ደግሞ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ውስጥ በስርቆት ተወስዶ በምሥጢር ተቀመጦ ይገኛል።

በእነዚህ ፕላኔቶች ውስጥ ያሉ ፍጥረታትን በተለየ ቋንቋ እየሳቡ የምሥርን /የግብጽ/ ፒራሚዶችን የተሰሩ ሲሆን። የምሥር /የግብጽ/ ፓራሚዶች የተሰሩት በሰው ልጆች ሳይሆን ከነዚህ ፕላኔቶች በመጡት ፍጥረታት እንደሆነ መጽሐፈ ምሥጢር ዘአዶናይ ራፉኤል በተባለው መዝገብ ላይ ተጽፏል። እዛው ፒራሚዱ ውስጥ በምስጢርም ተቀርጾ ይገኛል።

እነዚህም ባለ ሥስት ማዕዘን ድንጋይ ያለስሚንቶና ያለጭቃ ሰው ሊሸከመው በማይችል በትልልቅ ድንጋይ ተነባብሮና ተደራርቦ በሚያስደነቅ ሁኔታ ታንጿል። የጥንት ስሟም ምሥር የተባለችውም ግብጽ ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች ትጠራ ነበር።

ኢትዮጵያ ውስጥም እንደ ምሥር /ግብጽ/ሀውልቶች/ ከብዙ ድንጋዮች ሳይሆን ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰሩ 700 ፒራሚዶች 600 የአክሱም አይነት ሀውልቶች ከነ ቤተ-መንግስታቸው እና ብዙ የላሊበላ አይነት ሀውልቶች ይገኛሉ። ይህም አንድ ግዙፍ ከተማ ማለት ነው።

ነገር ግን እነዚህን ሀውልቶች ኢትዮጵያኖች አስቀብረዋቸዋል። እነዚህም ከተማዎች የጥንቷን ኢትዮጵያ ጥበብ ሸክፈው ይዘዋል። እነዚህን ሀውልቶች የት እንደሚገኙና በስንት ሜትር እርቀት ቆፍሮ ማውጣት እንደማቻል ዋልድባ ባለው መዝገብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ነገር ግን ጊዜው እስኪደርስ በምስጢር ተይዟል።

ለምሳሌ ያህል ደግሞ በቅርቡ በቁፍሮ የወጣውን የዳግማዊ ላልበላን ሀውልት ማየት ይቻላል። ዮሐንስ በራእዩ ሲከፈት ያየው ቤተ-መቅደስ እነዚሁ የላልበላን ሀውልቶች እንደሆኑ አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ ያስረዳሉ።

እንደ ምንጭነት የተጠቀሰውም የምሥጢሮች ሁሉ ቁልፍ  የሆነው መጽሐፈ ምሥጢር ዘአዶናይ ራፉኤል ሲሆን ይህም መጽሐፍ እጅግ በጣም ብዙ ምሥጢሮችን የያዘ ሲሆን መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ ቢተረጎም እጅግ በጣም የሚያሥፈራና አስደንጋጭ ታይቶና ተስምቶ የማይታወቅ ከሰው ልጆች በላይ የሆነ ምሥጢር አለው፤ ሁሉም ነገር እንደ ፈጣሪ ፍቃድ በጊዜው ይሆናል። የተለየ መንፈሳዊ አይን ያለው ሰው ግን አሁንም እነዚህን የፒራሚድ ከተሞች መመልከት ይቻላል።

ምንጮቸ ፦ የሊቁ አባ ተስፍ ሥላሴ ሞገስ   you tube video

ሔኖክ ዘአዶናይ

በየቀኑ የምንለቃቸው ጽሑፎች እንዲደርሷችሁ ለዚህ ቻናል አዲስ የሆናችሁ Join በማድረግ ተቀላቀሉን።

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5