Get Mystery Box with random crypto!

ከፈላስፋዎች ጉያ ያለምጥ መልካም ነገር አይወለድም የሰው ልጅ ለአምላኩ ያለው ጥያቄ ብዙ | Yoni Arts

ከፈላስፋዎች ጉያ

ያለምጥ መልካም ነገር አይወለድም

የሰው ልጅ ለአምላኩ ያለው ጥያቄ ብዙ ነው። አንደኛው ዛሬ ዝናቡን አዝንብልን ሲለው ሌላኛው ዛሬ መንገድ አስቤያለሁና አደራህን ያን ዝናብ ያዝልን ይለዋል። ታድያ አንድ ቀን አንድ ጎበዝ ገበሬ እግዚአብሔርን ሃሳቡን እንዲህ ሲል አማከረው ፦ "ይኸውልህ ጌታዬ እኔ እድሜዬን ሙሉ የግብርና ስራ የሰራሁ ብዙ ልምድ ያለኝ የታወቅኩ ጎበዝ ገበሬ ነኝ። ብዙ ጊዜ እንደዚህ አስባለሁ ፦ አምላካችን ስንዴ ከዘራን በኋላ በተገቢው ሰዓት ዝናብ ቢያዘንብልን ሃይለኛ ንፋስ ባይነፍስ እና የስንዴ ሰብላችንን በሐይል እየነቀነቀ ባይሰባብርብን ባያስቸግርብን ፤ አንዳንዴም ውርጭና ብርዱ ሰብላችንን ባያበላሽብን በአንድ አመት የምንሰበስበው ብቻ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት አለስጋት ያኖረን ነበር።  ታድያ ደጉ ጌታ ሰብላችንን እስክንሰበስብ ሁሉን ነገር ምቹ ለምን አታደርግልንም " አለው

እግዚአብሔርም የገበሬውን ንግግር አዳምጦ "እሺ እንደፈለግህ ይሁን " አለው። አመቱን ሙሉ የተዘራው ስንዴ ዝናብ ሳያጣ ንፋስ ሳያስቸግር ሁሉ ነገር እንደተደላደለ ሰብሉ በምቾት አደገ። ገበሬው እንዳለው ስንዴው ረጃጅም እና በጣም ብዙ ሆኗል እርሻው ላይ የሚያጓጉና ለዓይን ያማረ ነው ። ገበሬውም ይኸው ያልኩት ደረሰ አለ ።

በመጨረሻ የመሰብሰብያው ጊዜ ደርሶ ገበሬው ሰብሉን መሰብሰብ ሲጀምር በተመለከተው ነገር ከፉኛ ደነገጠ። ስንዴው ምንም ዘር የለውም። ገበሬው ግራ ተጋባና እግዚአብሔርን ጠየቀ "እንዴት ሊሆን ቻለ ?" እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ "አንተ አኮ በጭራሽ ስለ ንፋስ ስለውርጭ ስለማዕበል አልጠየክም ፤ አንተ የጠየከው ምቾትን ብቻ ነው ፤ የትኛውንም ነገር ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርጉት ጠንክሮ ዘርን አንዲይዝ የሚያደርጉት ተግዳሮቶች ናቸው ። መከራ ነው ስሩን ጠንካራ የሚያደርገው መነቅነቅ ነው ግንዱን የሚያፀናው በምጥ ነው ያማረ ነገር ሀሉ የሚወለደው"  አለው።

ወርቅ ተፈላጊነትን ያገኘው በእሳት ተፈትሎ ነው። እናም ፈተና ህይወታችንን ያጠነክረዋል እንጂ አያላላውም ተስፋችንን ያገዝፈዋል እንጂ ህልማችንን አያጨናግፍም ስለዚህ በህይወታችን ውስጥ የሚገጥሙን ፈተናዎች ፍሬያማ ሊያደርጉን ነውና ትኩረታችንን ዓላማችን ላይ ማድረግ ያስፈልጋል።

በየቀኑ የምንለቃቸው ጽሑፎች እንዲደርሷችሁ ለዚህ ቻናል አዲስ የሆናችሁ Join በማድረግ ተቀላቀሉን።

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5