Get Mystery Box with random crypto!

አልበርት አንስታይን እና ስራዎቹ ተጽእኖ ፈጣሪው አልበርት አንስታይን በማርች 14 በ1879 አ | Yoni Arts

አልበርት አንስታይን እና ስራዎቹ

ተጽእኖ ፈጣሪው አልበርት አንስታይን በማርች 14 በ1879 አ.ም ከአይሁዳዊ ቤተሰብ ነበር የተወለደው። አልበርት አንስታይን ከፈጠራቸው ፈጠራዎች መካከል ዋናዎቹ E=mc2, Relative theory, እና Gravity wave ናቸው። በልጅነቱ ደካማ የነበረው አልበርት አንስታይን በአእምሮው ጉብዝና ነበረበት። ይህ አልበርት አንስታይን የ2ኛ ደረጃ ትምክህቱን ባያጠናቅቅም በኤሌትሪክ ምህንድስና ትምህርት በዲግሪ ለመመረቅ ማመልከቻ አስገባ። ምንም እንኳን የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ባያጠናቅቅም ካለጸ መማር እንደሚችል የተገለፀለት። በውጤቱም በሒሳብ እና በፊዚክስ ውጤቱ አሪፍ የነበረ ቢሆንም በሌላው ትምህርት ዝቅተኛ በመሆኑ ማለፍ አልቻለም ነበር። ለማለፍም ብቸኛ አማራጭ የነበረው እንደገና የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ማጠናሸቀቅ ነበር። በትምርትቤቱም ታይቶ በማይታወቅ ነጥብ ነበር ያለፈው። (ለዚህም ነው 'ከትላንት ተማር, ዛሬን ኑረው, ነገን ተስፋ አድርግ, ግን ከዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ መጠየቅህን አታቁም')

E=mc2 የሚለው ቀመር ሰው ሁሉ ያውቃል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህ ያልተወሳሰበ የሚመስለው ይህ ቀመር የአልበርት አንስታይንን አስገራሚ ጭንቅላት ያሳያል። ይህ ፎርሙላ በአጭሩ በአንድ ነገር ውስጥ ያለ የታመቀ ኃይል (energy) መጠኑ የነገሩ ክብደት (mass) ሲባዛ ከብርሀን ፍጥነት እርስ በርሱ ሲባዛ (the speed of light squared) ማለትም Energy= mass (M) × Speed of light (C) × Speed of light (C). ክብደትን ወደ ሀይል ወይንም ሀይልን ወደ ክብደትን በመቀየር ነው። ይህንን ቀመር አልበርት አንስታይን ለአለም ቢያስተዋውቅም በዚህ ቀመር ተጠቅመው የኒውክለር ኃይልን ለአለም ያስተዋወቁት ሁለት ጀርመናዊ ሳይንትስቶች ናቸው።

ይህም በሌላ አገላለፅ አንድ ቁስ በብርሀን ፍጥነት መጓዝ ቢችል የቁሱ ክብደት በዚያው መጠን ይጨምራል። ስለዚህም አንድን ነገር (the speed of light squared) ማስኬድ ብንችል እቃው ግዙፍ ይሆናል ማለት ነው። ይህንን ስንል ሌላ ክብደት ይጨምርለታል ማለት አይደለም። apparent mass እና በጉዞ ላይ ያለው ክብደት (relativistic mass ) ስለሚለያይ ነው።

የብርሀን ፍጥነት በላይ መጓዝ ማለት ሽጉጥን ሳንተኩስ እንደ መተኮስ ማለት ነው። ማለትም የብርሀን ፍጥነት በሰኮንድ 300ሺ ኪ.ሜ ይጓዛል ማለት ነው። ይህንን ስንል ስለ እምነት ነው የምናወራው። በፊዚክስ ህግ ፀጉራችንን በሚሊየኖች እጥፍ ቢቆራረጥ ያቺ አንዷ ፀጉር (matter) ተብሎ ነው የሚጠራው። ልክ እንደ ዚች matter ካልሆነ በቀር በብረሀን ፍጥነት መጓዝ አይችልም።

ይቀጥላል ...

በየቀኑ የምንለቃቸው ጽሑፎች እንዲደርሷችሁ ለዚህ ቻናል አዲስ የሆናችሁ Join በማድረግ ተቀላቀሉን።

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5