Get Mystery Box with random crypto!

አይሁድና አእምሮው ከመላው ዓለም ሕዝብ ረገድ አይሁድ የዓለምን 0.2 በመቶ ብቻ የሕዝብ ድርሻ | Yoni Arts

አይሁድና አእምሮው

ከመላው ዓለም ሕዝብ ረገድ አይሁድ የዓለምን 0.2 በመቶ ብቻ የሕዝብ ድርሻ አለው፡፡ በእውነቱ እጅግ አነስተኛ ቍጥር ነው። ይኹን እንጂ ከ1901 እስከ 2020 ዓ/ም ባሉት 119 ዓመታት ውስጥ 900 የሚያኽሉ ሰዎች የኖቤል ሽልማትን አሸናፊነት ሲቀዳጁ ከእነዚያ ተሸላሚዎች ውስጥ 204 የሚኾኑቱ አይሁድ ናቸው፡፡ እንግዲህ ከሕዝባቸው አነስተኛ ርቢ አንጻር ለዚህች ዓለም ያበረከቱት አስተዋፅኦ ሲታሰብ (ሲብሰለሰል) ከሚጠበቀው በላይና በእጅጉ የላቀ ነው ያሠኛል፡፡

በሰላም 9 ፥ በኬሚስትሪ 36 ፥ በኢኮኖሚክስ 33 ፣ በሥነ ጽሑፍ 15 ፥ በፊዚክስ 55 ፣ በሥነ ሕይወትና በሕክምና 56 ፤ በጥቅሉ 204 አይሁድ በየዘርፉ የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል፡፡ ለምሳሌ ያኽል በአያሌው የሚታወቁቱ፡— አልበርት አንስታይን (ፊዚክስት) ፥ ኔልስ ቦህር (ፊዚክስት) ፥ ሲግመን ፍሬድ (ሳይካትሪስት) ፣ ፍሪትዝ ሐበር (ኬሚስት) ፣ ሮሳሊንድ ፍራንክሊን (ባዮሎጂስት) እንዲሁ በሰላም ዘርፍ ያሸነፉት የእሥራኤሉ ጠ/ሚር ሚናሒም ቤጊንና ሺምዖን ፔሬትዝ የሚጠቀሱት ናቸው።

የአይሁድ ሳይንስ አዋቂያን ጭንቅላታቸውን (ጭንቅ—አልላት) በአግባቡ አውጠንጥነው በዓለም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በመፍጠር በተለይም ደግሞ የኹሉ በኾነው በሳይንሱ መስክ ላይ ያበቀሉት ሳይንሳዊ ዘር ፥ የሰው ልጅ የሚኖርባት ዓለም ረቂቅ ጥበብን እንድትጐናጸፍና የኋላ ቀር ኑሮ ቅዝቃዜ ዐጥንቷን እንዳይቈረጥመው አድርገዋል። በአንጐላቸው አብላልተው ካመጠቋቸው አይጠገቤ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችም የተነሣ ሳይንስን ለአፍታ ሳይምሩ እንደ ኳስ አንዴ ወዲህ ፥ አንዴ ወዲያ እያንከባለሉ ምስጢሩን ኹሉ አዘርግፈውታል ቢባል የሚጋነን አይኾንም !

የአዳም ልጅ ኹሉ የአውሬ ባሕርይ በተላመደበት በክፉው ዘመን ዐይናችኹን አልያችኹ የተባሉት አይሁድ ኑሯቸው የኢትዮጵያ አበው (አባቶች) እንደሚተርቱት ያለ ኾኖባቸው ነበር። አበው ኢትዮጵያውያን ሲተርቱ “ብዕር ዘኢተፈጸመ ዐጸባሁ ወእምድኅረ ዘሞተ ይጠፈር ቍርበቱ ለከበሮ” ይላሉ። “መከራው ያላለቀለት በሬ ከሞተም በኋላ ቆዳው ለከበሮ ይጠፈራል” ማለታቸው ነው። ምንም እንኳ የዓለም ልጆች ኹሉ በየአጽናፉ ‘አክ ፥ እንትፍ’ ቢሏቸው የአእምሯቸው ውጤት የኾነውን ብስል ፍሬ አላምጠው ወደ ከርሣቸው ለመዶል ግን አሻፈረኝ ማለት አልቻሉም ! እጅጉን ይጣፍጣልና።

እንሆ በዓለም ብረት (ብሌን) ሲታዩ እንደ ሕዋስ እጅጉን ንኡሳን የኾኑ እኚህ ምስኪናን አይሁድ አስደማሚ ግብር የገበሩ የዕውቀት አለቃ በመኾናቸው እንደ አገር ፈርጣማና ጕልበታም ኾነው እንዲታዩ አብቅቷቸዋል።

ምንጭ:- መጽሐፈ ገጽ (ፕኒኤል)

በየቀኑ የምንለቃቸው ጽሑፎች እንዲደርሷችሁ ለዚህ ቻናል አዲስ የሆናችሁ Join በማድረግ ተቀላቀሉን።

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5