Get Mystery Box with random crypto!

ከብራና ገጾች መጽሐፈ አክሲማሮስ እና አልበርት አንስታይን የአልበርት አንስታይን (E=mc | Yoni Arts

ከብራና ገጾች

መጽሐፈ አክሲማሮስ እና አልበርት አንስታይን

የአልበርት አንስታይን (E=mc^2) ቀመር በኢትዮጵያን መጻሕፍት ላይ ተገኘ!!!

አልበርት አንስታይን ሁለት ቲዎሪዎችን አስቀምጧል። አንደኛው general relativity እና spiale relativity ሲሆኑ አጠቃላይ ሀሳቡ በብርሀን ፍጥነት በምንኖርበት ሁኔታ ላይ የጊዜ ልዩነት እንደሚኖር ያስረዳበት ነው። ይህ ቲዎሪ አልበርት 1905 እ.አ ነበር ያገኝው ነገር ግን የኛ አባቶች በአራተኛው ክፍለ ዘመን ከአልበርት 1600 አመታት በፊት ነበር በመጽሐፈ አክሲማሮስ ላይ እንዲህ በማለት አባቶቻችን የጻፉት"

በላይ ሰማይ ሳይ መላእክት ሲሰግዱ አየሁ እነሱ አንድ ሰዓት ሰገዱ በምድር ደግሞ 83 አመት አለፈ " ብርሀን ባለበት ቦታ ጊዜ ይፈዛል ማለት ብርሀን ያለበት ቦታና ብርሀን የሌለበት ቦታ ሰዓት የተለያየ ነው። እንዲሁም speed (ፍጥነቱ) ይለያያል። አንስታይ "time dilution and speed" የሚለው ይህን ነው።

black hole ምሥጢራት ላይ ለሚደረገው ጥናት ለምእራባውያኑ ፍንጭ የሰጠው Einstein's general relativity (GR) ንድፈ ሃሳብ ቢሆንም ከአልበርት አንስታይን ንድፈ ሃሳብ በተሻለ ግን ስለቦታዎቹ ማብራራት የሚቻለው መጽሐፈ ራዚኤል ወይም የሕይወት መጽሐፍ ተብሎ በሚጠራው መጽሐፍ ሲሆን ይህ መጽሐፍ በአራቱ ሰማያት መካከል ያለውን የኃይል የጊዜ እና የግዝፈት ልዩነት ያስረዳል፡፡

የዚህችን ዓለም ምሥጢራትና ጥበባት እና በውስጧ ያሉትን የተለያዩ ስውር ሀብታት 12ቱን ወር ሦስት ሦስት ወር በመከፋፈል የሚጠብቁ መላእክት አሉ፡፡ የነገድ አለቃቸው ራዚኤል የተባለ መልአክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አናንኤል ይባላል፡፡

ታዲያ አዳም በድሎ ወደ ምድር ሲመጣ ይህ መልአክ አዳም የምድርን ምሥጢራትና ጥበባት ይጠቀም ዘንድ በዚች ምድር ላይ ስለሚገኙት ምሥጢራትና ጥበባት በመጽሐፍ አዘጋጅቶ ቢሰጠውም ፈቃደ እግዚአብሔርን ባለመጠየቁ ሌሎች መላእክት ይህን መጽሐፍ ከአዳም ተቀብለው ወደ ምድር ይወረውሩታል። በቀጥታም ይህ መጽሐፍ ግዮን የተባለ ወንዝ ውስጥ ይወድቃል። ይህ ግዮን የተባለው ወንዝ የኛው አባይ ነው፡፡ ከወደቀ በኋላ መልአኩ ራዚኤል ከእግዚአብሔር ይቅርታን በማግኘቱ ይህን መጽሐፍ አዳም ተመልሶ ሊያገኘው ችሏል፡፡

መረጃዎች እንደሚያስረዱት ይህን መጽሐፍ ከአዳም ቀጥሎ ኖህ ከኖህ ሔኖክ ከሔኖክ ደግሞ ጠቢቡ ሰሎሞን እጅ የደረሰ ይህም መጽሐፍ በመላኩ አማካኝ ተጽፎ ለአዳም የተሰጠ መጽሐፍ ሲሆን አዳም የእሳት ዓለማት ውስጥ የሚገኙት ቅዱሳን መላእክት ያስተማሩትን ጥበብ ያሰፈረበት ነው፡፡

አዳም እኛ በምንኖርባት ምድር እና በገነት መካከል ያለውን የኃይል የጊዜ እና የግዝፈት ልዩነት ውጭ ሆኖ በሁለቱም ዓለማት ላይ መኖር የቻለው መላእክቱ ባስተማሩት ጥበብ ይህም አዳም ገነት በኖረበት ሰባት ዓመት እና በምድር 2555000 ሚሊዮን ዓመት መካከል ያለውን የኃይል የግዝፈት እና የጊዜ ልዩነት አስማምቶ መኖር ችሏል፡፡

በዚህም መሰረት አዳም ወደ ምድር ሲመጣ ሰባት አመት እንዳሳለፈ ሰው እንጂ በምድራዊ የጊዜ አቆጣጠር 2555000 ሚሊዮን ዓመት እንዳሳለፈ ሰው ሆኖ አይደለም ወደ ምድር የመጣው፡፡

ለዚህ ቻናል አዲስ የሆናችሁ Join በማድረግ ተቀላቀሉን።

ምንጭ:- ፩ መጽሐፈ አክሲማሮስ

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5