Get Mystery Box with random crypto!

የብእር ትሩፋት ምርኮኛ አለቃ እንጅ ፀባይ አይቀይርም? አሌክስ አብርሃም እንደፃፈው | Yoni Arts

የብእር ትሩፋት

ምርኮኛ አለቃ እንጅ ፀባይ አይቀይርም?

አሌክስ አብርሃም እንደፃፈው

ዛሬ ላይ በተለይ የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኞች ስለህወሀትና ብልፅግና ሲዘግቡ ትዝ የሚለኝ ደራሲ ተስፋየ ገብረዓብ ነው!ነፍስ ይማር! እንጀራ ሁኖበት ጦር ሜዳ ወርዶ ለደርግ ፕሮፖጋንዳ ሲሰራ "አገር ገንጣዩ ፣ በአረብ ፔትሮል ገንዘብ የጠገበው አገር ሻጩ ወያኔ ሰላማዊ ዜጎችን በጭካኔ በመጨፍጨፍ ..." እያለ ! ወዲያው ተማረከ ! ተማረከና በዛ በኩል ሁኖ ለህወሀት ፕሮፖጋንዳ መስራት ጀመረ! ምን እያለ? " ፋሽቱ ፣ ሰው በላው ደርግ የኢትዮጵያ ጠላት ከሆኑ አገራት በሚያገኘው የመሳሪያ እርዳታ ሰላማዊ ዜጎችን በመጨፍጨፍ... " ሁለቱም ውሸት ነበር ይለናል በኋለኛው ዘመኑ በፃፋቸው ድርሳናት

እና ፈገግ የሚያደርገው ...በደርግም በህወሀትም በኩል የነበሩት የተስፋየ አለቆች ሁለቱም ስማቸው አበበ ነበር ..(ጀኔራል አበበ ኃይለሥላሴ እና ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት) በአበበዎች መሀል ስንት ሚስኪን በሶ አለቀ!

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5