Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ ልጆቻቸውን በምግባር በሃይማኖት እንዲያድጉ የማያደርጉ ወላጆች የልጆቻ | ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ ልጆቻቸውን በምግባር በሃይማኖት እንዲያድጉ የማያደርጉ ወላጆች የልጆቻቸው ገዳዮች ናቸው፡፡ እስኪ ንገሩኝ! ለዔሊ ልጆች መሞት ተጠያቂው ማን ነው? እርሱ ራሱ አይደለምን? እርግጥ ነው የጠላት ጦር ልጆቹን ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡ የአባታቸው የዔሊ ደንታቢስነት ግን ጦሩ ልጆቹን አነጣጥሮ እንዲወጋቸው አድርጎታል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር ስለ ራቃቸው በፍልስጥኤማውያን ጦር ፊት እንዲቆሙ አደረጋቸው፡፡ በዚህም አባታቸው ራሱንም ልጆቹንም ገደለ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ይህንን ዕለት ዕለት በዓይናችን ፊት እያየነው ነው፡፡ የማይታዘዙትንና ሥርዐት የለሽ ልጆቻቸውን በአግባቡ መቅጣት የማይፈልጉ ወላጆች ስፍር ቊጥር የላቸውም! ልጆቻቸውን ጠንከር አድርገው መገሠጽን ይፈራሉ፡፡ የወላጆቹ እንደዚህ መኾንስ የሚያመጣው ውጤት ምንድን ነው? የልጆቹ ሥርዐት አልበኝነት ይጨምራል፡፡ አለመቀጣታቸው ወደ ዓመፃ ወንጀል ያመራቸዋል፡፡ ወደ ወኅኒ ይወሰዳሉ፡፡ ከዚህ እጅግ ከከፋም በሞት ይቀጣሉ፡፡ ወዮ! የራሳቸውንና የተፈቀደላቸውን የመቅጣት መብት ችላ በማለታቸው፥ ልጆቻቸውን ለከፋ ቅጣት አሳልፈው ይሰጣሉ፤ ሕዝባዊ ሕጉም ለራሱ የተፈቀደለትን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ እነርሱ (ወላጆቹ) እያዩአቸው በቀላል ቅጣት ሊያስተካክሏቸው ሲገባቸው፥ ይኸው ማንም አጠገባቸው በሌለበት አሰቃቂ ቅጣት ይፈጸምባቸዋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 162