Get Mystery Box with random crypto!

'ተስፋ አትቁረጪ፡፡ ኦሎምፒያስ ሆይ! እውነተኛውና እጅግ ክፉው ነገር አንድ ብቻ ነው፤ እውነተኛ ፈ | ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ተስፋ አትቁረጪ፡፡ ኦሎምፒያስ ሆይ! እውነተኛውና እጅግ ክፉው ነገር አንድ ብቻ ነው፤ እውነተኛ ፈተና አንድና አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ኃጢአት ነው፡፡ እንዲህ ብዬ አሰምቼ መንገሬንም መቼም መች አላቋርጥም፡፡ ሌሎች ነገሮች ግን - ለምሳሌ ሴራዎች፣ ጥላቻዎች፣ ማጭበርበሮች፣ ሐሜቶች፣ ስድቦች፣ ወቀሳዎች፣ የራስ ያልኾነን ነገር የእኔ ነው ብሎ መያዝ፣ ስደት፣ ስል የኾነ የጠላት ጎራዴ፣ የጉድጓድ ውስጥ የኾኑ አደጋዎች፣ ከዓለም ኹሉ የሚመጣ ውጊያ፣ እንዲሁም አንቺ ልትጠሪው የምትችዪ ሌላም ኹሉ ነገር - እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡ የእነዚህ ነገሮች ክብደታቸው ምንም ይኹን ምን ሐላፊያን ናቸው፤ የሚጠፉ ናቸው፤ ሟች ሰውነታችንን ሊጎዱ ቢችሉም እንኳን መንፈሳዊው ማንንታችንን ግን ምንም ሊያደርጉ የማይችሉ ናቸው፡፡ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስም ከዚህ ዓለም ሕይወት ጋር ተያይዘው የሚገኙ ደስታዎችም ኾኑ ኀዘኖች ምናምንቴነትን ሊናገር ወድዶ እውነቱን በአንዲት አረፍተ ነገር ገልጦታል፤ እንዲህ ሲል፡-“የሚታዩ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸውና” /2ኛ ቆሮ.4፥18/፡፡ ታዲያ እንደ ፈሳሽ ውኃ የሚያልፉ ጊዜያዊ ነገሮችን የምትፈሪው ስለ ምንድን ነው?

@ ወደ ኦሎምፒያስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ