Get Mystery Box with random crypto!

ፊልጵ.4፡1፣ 1ኛ ቆሮ.10፡33)፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን ሞትን እንደ ናቁት ወደ እቶኑ እሳትም ኾ | ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ፊልጵ.4፡1፣ 1ኛ ቆሮ.10፡33)፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን ሞትን እንደ ናቁት ወደ እቶኑ እሳትም ኾነ ወደ አንበሳ ጕድጓድ ሲጣሉ ምንም ምን ባለመፍራታቸው ግልፅ ኾኖአል፡፡ ኹልጊዜ ግን ድል መንሣት ይፈልጉ የነበረው በረድኤተ እግዚአብሔር ነበር፡፡ ቀጥለውም እግዚአብሔር ይህን እንዲያደርግላቸው ሲለምኑት፥ እነርሱ ራሳቸው እርሱን ለመለመን የተገቡ እንዳልኾኑ በማሰብ ይጸልዩ የነበረው “ስለ ባለሟልህ ስለ ይስሐቅና ስለ ወዳጅህ ስለ አብርሃም ስላከበርኸውም ስለ ያዕቆብ” በማለት ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ኪዳን በማሳሰብ ነበር (መዝ.ሠለ.ደቂ. ቊ.11)፡፡ እነርሱ ራሳቸው ለእግዚአብሔር ያቀርቡት የነበረው ግን አንድ ነገር ብቻ ነበር - “የተሰበረ መንፈስ” (ቊ.16) !

እንግዲያውስ እነዚህን ወጣቶች አብነት እናድርጋቸው፡፡ ዛሬም በፊታችን የቆመ የወርቅ ምስል፥ እንዲያውም ከዚህም የከፋ የገንዘብ ሐውልት አለና፡፡ ነገር ግን በዙሪያ ኾኖ የሚሰ’ማውን የከበሮውንና የእምቢልታውን፣ የበገናውን ወይም የገንዘብ ሐውልትን በዓል አድማቂዎችን ድምፅ አንስማ፡፡ አዎን፥ ወደ “ድኽነት እቶን” ውስጥ ብንገባም እንኳን ለዚህ ጣዖት ላለመስገድ እንቁረጥ፤ ያን ጊዜም “የእሳቱ ነበልባል እንደ ቀዘቀዘ ነፋስ” ይኾንልናል (ቊ.25)፡፡ ስለዚህ ስለ “ድኽነት እቶን” በሰማን ጊዜ አንራድ፤ አንንቀጥቀጥም፡፡ በባቢሎኑ እቶን እሳት አማካኝነት ክብርን የተጎናጸፉት እነዚያ ወደ እቶኑ የተጣሉት ሠለስቱ ደቂቅ ናቸው፡፡ ወላፈኑ ያቃጠላቸው ከእቶኑ እሳት ውጭ የነበሩትና ለወርቅ ምስሉ የሰገዱት ናቸውና፡፡ ለገንዘብ ሐውልት ለሚሰግዱ ሰዎች የእሳቱ ወላፈን የሚያገኛቸው አንዳንዶቹን በዚህ ዓለም ነው፤ ሌሎቹን በወዲያኛው ዓለም ነው፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ነው፡፡ ለገንዘብ ሐውልት ከሚሰግዱ ይልቅ የድኽነትን እቶን የመረጡ ግን በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይሾማሉ፤ ይሸለማሉና፡፡ በዚህ ዓለም አለአግባብ ባለጠጋ የኾኑትም በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ፍዳ ያገኛቸዋልና፡፡
አልዓዛር ከዚህ ከ “ድኽነት እቶን” ውስጥ ገብቶ ሠለስቱ ደቂቅ ካገኙት ክብር ይልቅ ይበልጥ ክብርን አግኝቶአል፡፡ ባለጠጋው [ነዌ] ግን ለወርቅ ምስሉ እንደ ሰገዱትና በወላፈኑም እንደ ጠፉት ሰዎች፥ እሳተ ገሃነም አገኘው (ሉቃ.16፡23)፡፡ የሠለስቱ ደቂቅና በወላፈኑ እሳት የሞቱት ሰዎች ምሳሌነታቸው ለዚህ ነበርና፡፡ ስለዚህ ሠለስቱ ደቂቅ ወደ እቶኑ እሳት በተጣሉ ጊዜ የእሳቱ ነበልባል ምንም እንዳልነካቸውና ይልቁንም ጽኑዓን እንደ ኾኑ ኹሉ፥ ለገንዘብ ጣዖት ላለመስገድ ወደ “ድኽነት እቶን” ውስጥ የሚጣሉትም ዕጣ ፈንታቸው ጽዋ ተርታቸው በወዲያኛው ዓለም በመንግሥተ ሰማያት ጽኑዓን ኾነው መኖር ነው፡፡ በፈለገ እሳት (በእሳት ጅረት) የሚኼዱ ቅዱሳን ሕማም እንደማያገኛቸውና ይልቁንም ደስ እንደሚሰኙ ኹሉ፥ ለዚህ ምስል የሰገዱ ግን የእሳቱ ወላፈን ከየትኛውም አርዌ ምድር በላይ በላያቸው ላይ ሲከመር፥ ወደ ራሱም ጎትቶ ሲያቃጥላቸው ያዩታል፡፡ ስለዚህ እሳተ ገሃነም መኖሩን የሚጠራጠር ሰው እርሱ አሁን የሚደረጉትን ተመልክቶ ሊመጣ ያለውን ከማመን አይዘግይ፡፡ ከ “ድኽነት እሳት” በላይም የኃጢአትን እሳት ይፍራ፤ ይንቀጥቀጥም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት እሳትም ሥቃይም የኃጢአት እሳት ነውና፤ የድኽነት እሳት ግን ጠልና ዕረፍት ነውና፡፡ ከኃጢአት እቶን ጋር ያለው ዲያብሎስ ነውና፤ በድኽነት እሳት ውስጥ ግን ያሉት ነበልባሉን የሚያጠፉ ቅዱሳን መላእክት ናቸውና፡፡

@የማቴዎስ ወንጌል፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.4፥18-19